\”ቤትኪንግ ኢትዮጵያን ለቆ የወጣው በራሱ አስተዳደራዊ ምክንያት ነው።\” አቶ ክፍሌ ሰይፈ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የስያሜ ባለቤት የሆነው ቤትኪንግ ከሀገር የወጣበትን ምክንያት ከአኪሲዮን ማህበሩ ሥራ አስኪያጅ አጣርተናል።

\"\"

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የስያሜ ባለቤት የሆነው ቤትኪንግ በትናንትናው ዕለት የሊጉ አክስዮን ማኅበር የቦርድ አባላት ምርጫ ባካሄደበት ወቅት በድጋሚ የቦርዱ ሰብሳቢ በመሆን የተመረጡት መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ \”ቤትኪንግ ኪሣራ አስተናግዶ ከሀገር ወጥቷል\” ማለታቸውን ተከትሎ በርካታ ዘገባዎች ሲወጡ የቆየ ሲሆን ምክንያቱን ለማጣራት የአክሲዮን ማኅበሩን ሥራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈን ጠይቀናል።

እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለፃ ከሆነ ቤትኪንግ ከሀገር የወጣበት ምክንያት ግልጽ ባይሆንም በታክስ ፣ በቴሌቪዥን እና መሰል ጉዳዮች በራሱ አስተዳደራዊ ምክንያት መሆኑን ከሀገር ከወጣም ከሦስት ወራት ያላነሱ ጊዜያት እንዳለፉ እና በሊጉ የስያመ መብት ስምምነት ላይም ሌላ ይግባ የሚል እንደሌለ እና እስከያዝነው ዓመት መጨረሻ ያለው ክፍያው መፈፀሙን ነግረውናል።

አቶ ክፍሌ አክለውም \”ቤትኪንግ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሱቅ ዘግቶ ከሥራ ወጥቷል። ነገር ግን ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክስዮን ማኅበር ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም ፤ የሚያመጣው ተፅዕኖም የለም። በሜዳ እና በተመልካች እጦት ምክንያት ነው የወጣው የሚባለው ሀሰት ነው ፤ ስያሜውም ባለበት ይቀጥላል ።\” ብለዋል።

\"\"