ከፍተኛ ሊግ | የ16ኛ ሳምንት የዛሬ ውሎ

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በምድብ \’ሀ\’ በዝናብ ምክንያት ሁለት ጨዋታዎች ወደ ነገ ሲዘዋወሩ በምድብ \’ሐ\’ ሦስት ጨዋታዎች ተከናውነዋል።

\"\"

አሰላ ላይ እየተከናወነ የሚገኘው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የምድብ \’ሀ\’ ውድድር ረፋድ ላይ ሀላባ ከተማ እና ወልዲያን ያገናኘ ሲሆን ጨዋታው ግብ ሳይቆጠርበት ተጠናቋል። በመቀጠል አዲስ ከተማ ክ/ከ እና ቡታጅራ ከተማ እንዲሁም ወሎ ኮምቦልቻ እና ባቱ ከተማ ሊያደርጓቸው የነበሩ ጨዋታዎች ግን በዝናብ ምክንያት ሳይካሄዱ ቀርተዋል። በመሆኑም የመጀመሪያው ጨዋታ ነገ 03:00 ሁለተኛው ደግሞ 05:00 ላይ እንዲከናወኑ አወዳዳሪው አካል ወስኗል።

\"\"

የምድብ ሐ ጨዋታዎች

ቡራዩ ከተማ 2-1 ነጌሌ አርሲ

በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ጥሩ የሚባል እንቅስቃሴ ያሳዩ ሲሆን በነጌሌ አርሲ በኩል ሰለሞን ገመቹ እና ዝነኛው ጋዲሳ የመሀል ክፍሉን በጥሩ ሁኔታ በመቀናጀት ጥሩ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ተስተውሏል። በማጥቃቱ በኩልም አበዱልሀኪም ሱልጣን እና ምስጋናው ሚኪያስ ጥሩ የሚባሉ እና ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ሲያከናውኑ ተመልክተናል። ቡራዩ ከተማ በኩል በመሀል ሜዳው ሱራፌል ተሾመ እንዲሁም መሀመድ ከድር ከመሀል ሜዳ የሚነሱ ግሩም ግሩም ኳሶችን ወደ ፊት በማሻገር የግብ ዕድሎች እንዲፈጠሩ ትልቅ አስተዋፅኦ ሲያደረጉ የፊት መስመሩን ደግሞ አኗር ሙራድ በጥሩ ሁኔታ የነጌሌ አርሲን የተከላካይ ክፍል ሲፈትን ቆይቷል። በ37ኛው ደቂቃ ቡራዩ ከተማዎች በጥሩ ቅብብል ያገኙትን ኳስ  ሙሉጌታ ካሳሁን በግሩም ሁኔታ በማስቆጠር መሪ ማድረግ የቻለ ሲሆን ብዙም ሳይቆይ በ42ኛው ደቂቃ የነጌሌ አርሲዎች አለመረጋጋትን ተጠቅመው ቡራዩ ከተማዎች በለገሰ ዳዊት አማካኝነት በማስቆጠር የግብ ልዩነቱን በሁለት በማሳደግ ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።

\"\"

ሁለተኛው አጋማሽ ነጌሌ አርሲዎች በመጀመሪያው አጋማሽ ያሳዩትን ደካማ አቋም ለማረም የተጫዋች ቅያሬ አድርገው የገቡ ሲሆን ለውጡንም ተከትሎ ነጌሌ አርሲዎች ቡራዩ ከተማዎችን ጫና ውስጥ በመክተት ግብ ለማስቆጠር ሲጥሩ ተስተውሏል። በ80ኛው ደቂቃ የነጌሌ አርሲው ተጫዋች ቱፋ ተሽቴ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። እንዲሁም የቡራዩ የተከላካይ ክፍል በጥሩ ሁኔታ የነጌሌ አርሲን ጫና በመቋቋም ግብ እንዳይቆጠርባቸው የቻሉትን ሲጥሩ የነበረ ሲሆን በ82ኛው ደቂቃ ነጌሌ አርሲዎች ያገኙትን ኳስ ወደ ግብ ክልል ሲያሻሙ ሲሳይ ሚደቅሳ በጭንቅላት በመግጨት አስቆጥሯል። ግቧም ነጌሌ አርሲን ከሽንፈት ሳይታደግ ጨዋታው በቡራዩ ከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል።

ሮቤ ከተማ 0-1 የካ ክ/ከተማ

የመጀመሪያው አጋማሽ ጥሩ የሚባል እና ኳስን መሰረት ያደረገ አጨዋወት በሁለቱም በኩል የተመለከትን ሲሆን በግብ ሙከራ እና በጨዋታ የየካ ክ/ከተማ የበላይነት ታይቷል። ሮቤ ከተማዎች በአብዱልአዚዝ ዑመር ጥሩ የሚባል የግብ ዕድል የፈጠሩ ቢሆንም በየካ ክ/ከተማዎች ግብ ጠባቂ እንዳሻው እሸቴ የባከነ ሲሆን እንደገና በአማኑኤል በቀል አማካኝነት ጥሩ ጥሩ ሙከራዎችን ሲያደርጉ አጋማሹም ያለ ምንም ግብ ተጠናቆ ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።

\"\"

ሁለተኛው አጋማሽ እንደ መጀመሪያው አጋማሽ ጥሩ እንቅስቃሴ የተመለከትን ሲሆን በሮቤ ከተማ በኩል የተሻለ አጨዋወትን ሲከውን በየካ ክ/ከተማ ደግሞ የኋላ መስመራቸውን በማጠናከር ጥሩ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ተስተውል። የካ ክ/ከተማዎች በተደጋጋሚ የሮቤ ከተማ ግብ በመድረስ የግብ ሙከራ ሲያደርጉ በ58ኛው ደቂቃ የሮቤ ከተማዎች የፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ጥፋት በመሰራቱ የተገኘውን ፍፁም ቅጣት ምት በኃይልሽ ፀጋዬ አማካኝነት ግብ በማስቆጠር የካ ክ/ከተማዎችን አሸናፊ ማድረግ ችሏል። ጨዋታውም በየካ ክ/ከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል።

ሶዶ ከተማ 0-0 ኮልፌ ክ/ከተማ

\"\"

የመጀመሪያ አጋማሽ ጥሩ እንቅስቃሴ እና አልፎ አልፎ የቆራረጡ ኳሶችን ያስተዋልን ሲሆን ነገር ግን ተመጣጣኝ የሆነ አጨዋወት ተመልክተናል። ኮልፌ ክ/ከተማዎች በኳስ ቁጥጥር እና ቶሎ ቶሎ ወደ ፊት በመድረስ የተሻሉ ሲሆኑ በአንፃሩ ሶዶ ከተማዎች ኃይልን ቀላቅለው በመጫወት ተጋጣሚያቸውን ጫና ውስጥ ለመክተት ሲሞክሩ ተስተውሏል።

ሁለተኛው አጋማሽ እንደ መጀመሪያው አጋማሽ ተመሳሳይ እንቅስቃሴ እስከ 70ኛው የተመለከትን ሲሆን ከ70ኛው ደቂቃ በኋላ ኮልፌ ክ/ከተማዎች የተጫወች ቅያሪ በማድረግ የተሻለ እንቅስቃሴ ማድረግ ቢችሉም በጨዋታው ምንም ግብ ሳይቆጠር ጨዋታው በአቻ ውጤት መጠናቀቅ ችሏል።

\"\"