ሪፖርት | ፈረሰኞቹ ነጥብ ጥለዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሲዳማ ቡናን ያገናኘው ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

\"\"

የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊሶሽ ከአሸናፊው ስብስባቸው አንድ ለውጥ ስያደርጉ ወደ ሜዳ ሲገቡ ሲዳማ ቡናዎች በበኩላቸው የሦስት ተጫዋቾች ለውጥ አድርገው በጀመሩት ጨዋታ ግብ የተስተናገደው ገና በሁለተኛው ደቂቃ ነበር። በዚህም ፍሊፕ አጃህ ደስታ ደሙ ከመስመር ያሻማውን ኳስ ሳላዲን ሰዒድ ጨርፎ አግኝቶት በግራ እግሩ ግብ በማስቆጠር ሲዳማን መሪ ማድረግ ችሏል።

 

\"\"

በአጋማሹ ከተጋጣሚያቸው በተሻለ የግብ ዕድሎች የፈጠሩት ሲዳማዎች በሳላዲን እና ፀጋዬ አበራ አማካኝነት ሙከራ ማድረግ ችለዋል። ሲዳማዎች በተለይም በግብ አስቆጣሪው ፍሊፕ አጃህ አማካኝነት በመልሶ ማጥቃት የፈጠሩት የግብ ዕድል ከተፈጠሩት ዕድሎች የላቀ ነበር።

በአጋማሹ በብዙ መለክያዎች ወርደው የታዩት ፈረሰኞቹ ዕድሎች ከመፍጠር ባለፈ ይህ ነው የሚባል ለግብ የቀረበ ሙከራ ማድረግ አልቻሉም።

\"\"

ከመጀመርያው አጋማሽ አንፃር ሲታይ በቁጥር ጥቂት ሙከራዎች የተመዘገበበት ሁለተኛው አጋማሽ በሁለቱም ቡድኖች በኩል የተደረጉ ሙከራዎች ጥቂት ነበሩ።

በጨዋታው ጥሩ የመከላከል አደረጃጀት የነበራቸው ሲዳማዎች ፍሊፕ አጃህ ከሳጥኑ ጠርዝ ባደረገው ሙከራ አማካኝነት መሪነታቸውን ለማስፋት ጥረው ነበር። ፈረሰኞቹ በበኩላቸው ናትናኤል ዘለቀ በግንባር ባደረገው ሙከራ አቻ ለመሆን ጥረት አድርገው ተስተውሏል።

\"\"

በሰማንያ ሦስተኛው ደቂቃም ተቀይሮ የገባው ዳግማዊ አርዐያ ቢኒያም በላይ በጥሩ መንገድ ያመቻቸለትን ኳስ ከሲዳማ ተከላካዮች ጋር ታግሎ በማስቆጠር ቡድኑን አቻ ማድረግ ችሏል። ጨዋታው ፈረሰኞቹ ግብ ካስቆጠሩ በኋላ ተጨማሪ ግብ ባለማስተናገዱ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

\"\"</a