ድሬዳዋ ከተማ አዲስ አሠልጣኝ በይፋ ሾሟል

ትናንት ድሬዳዋ ከተማን ለማሰልጠን ከጫፍ እንደደረሱ ገልፀን የነበረው አስራት አባተ በይፋ የክለቡ አሠልጣኝ ሆነዋል።
\"\"
በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚሳተፈው ድሬዳዋ ከተማ ክረምት ላይ ከሹመው አሠልጣኝ ዮርዳኖስ ዓባይ ጋር ከተለያየ በኋላ ወዲያው አዲስ አሠልጣኝ ለመሾም እንቅስቃሴ ጀምሮ ነበር። በዚህም ሦስት አሠልጣኞችን በእጩነት ይዞ የነበረው የክለቡ ቦርድም አስራት አባተን ለመሾም ወስኖ እንደነበር በትናንትናው ዕለት ዘገባ አቅርበን ነበር። አሠልጣኙም ከትናንት በስትያ አሁን ካለባቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ኃላፊነት ለመነሳት ለብሔራዊ ፌዴሬሽኑ መልቀቂያ አስገብተው የነበረ ሲሆን ከደቂቃዎች በፊት መልቀቂያቸውን ማግኘታቸው ተረጋግጧል።
\"\"
ትናንት ምሽት ከክለቡ ተጫዋቾች ጋር ትውውቅ ያደረጉት አሠልጣኝ አስራት መልቀቂያቸውን እንዳገኙ ወዲያው ይፋዊ ፊርማቸውን እንዳኖሩ ታውቋል። በዚህም እስከውድድር ዓመቱ መጨረሻ ድረስ የክለቡ አሠልጣኝ ሆነዋል። አሠልጣኙ ዛሬ ክለቡ ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር በሚያደርገው ጨዋታ የማይመሩ ሲሆን ለዛሬ ያለፉትን ቀናት ልምምድ ያሰሩት ምክትል አሠልጣኙ ሽመልስ በቦታው የሚሰየሙ ይሆናል።