ሀዋሳ ከተማ ቅጣት ተላልፎበታል


በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 24ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ላይ በታዩ የዲሲፕሊን ግድፈቶች ዙሪያ ውሳኔ ተላልፏል።

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሀዋሳ ከተማ ቆይታ ሁለት የጨዋታ ሳምንታትን ሲያስቆጥር በዚህ ሳምንት በተደረጉ ጨዋታዎች ላይም ታይተዋል በተባሉ የዲሲፕሊን ግድፈቶች ላይ ውሳኔ ማሳለፉን አወዳዳሪው አካል አሳውቋል።
\"\"
በክለቦች ደረጃ በታዩ ሪፖርቶች ከተላለፉ የተለያዩ ውሳኔዎች መካከል ሀዋሳ ከተማ በሳምንቱ ጨዋታ የተጋጣሚ ክለቡ ደጋፊዎችን እና የእለቱን ዳኛ በአምላክ ተሰማ አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት የቀረበ በመሆኑ የክለቡ ደጋፊዎች ለፈፀሙት ጥፋት ክለቡ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ብር 50000/ሃምሳ ሺህ/ እንዲከፍል ፥ አዳማ ከተማም የክለቡ ደጋፊዎች 2/ሁለት/ የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታድየም የተመልካች መቀመጫ ወንበሮችን ስለመስበራቸው ሪፖርት የቀረበ በመሆኑ ክለቡ የተሰበሩትን ወንበሮች እንዲያሰራ ወይም የዩኒቨርስቲው አሰተዳደር የሚያቀርበውን የንብረትን ዋጋ እንዲከፍል ተወስኗል፡፡
\"\"በተጨማሪም ለቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የቡድን መሪ እና ምክትል አሰልጣኝ አዲስ ወርቁ ፣ ለሀዋሳ ከተማ ክለብ የቡድን መሪ እና የደጋፊ ማህበር ተወካይ እንዲሁም ለሲዳማ ቡና ክለብ የቡድን መሪ እና የደጋፊ ማህበር ተወካይ በቀጣይ ቀናት ውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ለማነጋገር ጥሩ ማድረጉን አወዳዳሪው አካል አሳውቋል።