የአሰልጣኞች አስተያየት| ሀዋሳ ከተማ 2 – 2 ኢትዮጵያ መድን

\”የተቆጠሩብን ፍፁም ቅጣት ምቶች ዋጋ አስከፍለውናል\” ዘርዓይ ሙሉ

\”የቆመ ኳስ ሲገባብህ የጥንቃቄ ችግር ነበር ማለት ነው\” ረዳት አሠልጣኝ ለይኩን ታደሰ (ዶ/ር)

አራት ግቦች ያስተናገደው እና በአቻ ውጤት የተጠናቀቀው የሀዋሳ ከተማ እና መድን ጨዋታ ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለቱም ቡድን አሰልጣኞች ለሶከር ኢትዮጵያ የሰጡት አስተያየት እንደሚከተለው አቅርበነዋል።

ዘርዐይ ሙሉ – ሀዋሳ ከተማ

ስለ ጨዋታው…

ጨዋታው ማራኪ አልነበረም። የሚሰጡ ፍፁም ቅጣት ምቶች ይሁኑ አይሁኑ ቡድኑን እያወረዱት ነበር። ይጀምር እና በፍፁም ቅጣት ምቶቹ ይቋረጣል እንቅስሴው እንደፈለግነው አልሆነም። እነሱ ኳሱን ለመቆጣጠር ይሞክራሉ። እኛ ደግሞ እነሱ ትተውት የሚመጡ ቦታዎች ለመጠቀም ነበር የሞከርነው። የተቆጠሩብን ፍፁም ቅጣት ምቶች ዋጋ አስከፍለውናል፤ እኛም ከቆሙ ኳሶሽ ለመጠቀም ሞክረናል። ዛሬ ቡድናችን እንደ ፍላጎቱ አልተጫወተም።
\"\"
በተከላካይ ክፍል የታየው ክፍተት…

በዛ ክፍል ክፍተት የተፈጠረው ከሰባት ከስምንት ጨዋታ በኋላ ነው። በረከት ባለመኖሩ አዲስ ተጫዋች ነው የተጠቀምነው ፤ ክፍሉ ሚዛን አልነበረውም። የመጀመርያው ፍፁም ቅጣት ምት በመሸፋፈን ክፍተት የመጣ ነው፤ ሁለተኛው ግን ድጋሜ ማየት ይኖርብኛል። በቀጣይ ጨዋታ ችግራችን መፍታት እንችላለን።

ለይኩን ታደሰ (ረዳት አሠልጣኝ)

ስለ ጨዋታው…

ጨዋታው እንደጠበቅነው ነው። በሽግግር እና በቆሙ ኳሶች ልያጠቁን እንደሚችሉ ገምተን ነበር እንደጠበቅነው ነው የሆነው።

ስለ ዋንጫ ፉክክሩ…

ስለ እየንዳንዱ ጨዋታ ነው ምናስበው። እያንዳንዱ ጨዋታ ማሸነፍ የት ድረስ ይወስደናል የምናየው ይሆናል።
\"\"
ጎሎቹ የተቆጠሩበት መንገድ…

የቆመ ኳስ ሲገባብህ የጥንቃቄ ችግር ነበር ማለት ነው። ብዙ ጎሎች አግብተናል በዛ ልክ ደሞ ብዙ ግቦች አስተናግደናል። ግቦች ስናስተናግድ የመጀመርያችን አደለም። ለመጨረሻ ጊዜ ግብ ሳናስተናግድ የወጣነው ከስድስት ጨዋታዎች በፊት ነበር ፤ ተደጋጋሚ ጊዜ የሰራነው እና ማረም ያልቻልነው ችግር ነው።