ሁለት ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቡድኖቻቸውን አሸናፊ አድርገዋል

በMLS ጥሩ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘው ማረን ኃይለስላሴ እና ቤተ እስራኤላዊው ስንታየው ሳላሊች ግብ አስቆጥረዋል።

\"\"

👉 ማረን ኃይለስላሴ በምርጥ ብቃት ይገኛል

በጥር ወር በውሰት ውል የአሜሪካው ቺካጎ ፋየር ተቀላቅሎ ምርጥ ብቃት በማሳየት የሚገኘው ማረን ኃይለስላሴ ቡድኑ ከአትላንታ ዩናይትድ ጋር አቻ በተለያየበት ጨዋታ አንድ ጎል ስያስቆጥር ጆርጅዮ ኮትስያስ ባለቀ ሰዓት ላስቆጠራት ወሳኝ ግብም አመቻችቶ አቀብሏል። ከአንድ ጨዋታ በፊት ቡድኑ ሴንት ሎይስን ባሸነፈበት ጨዋታ ወሳኝ ግብ ያስቆጠረው ይህ የመስመር ተጫዋች ባሳየው ድንቅ ብቃት በሳምንቱ ምርጥ ቡድን መካተት ችሏል።

👉 ስንታየሁ ሳላሊች ግብ አስቆጠረ

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ቤተ እስራኤላዊ አጥቂ ስንታየሁ ሳላሊች የቡድኑ ያሸነፈበት ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል። ቡድኑ ዶክሳ ካቶኮፕያስ ባሸነፈበት ጨዋታ በሰባ ሰባተኛው ደቂቃ ተቀይሮ በመግባት በሰማንያ አራተኛው ደቂቃ ላይ የማሸነፍያ ግቡን ያስቆጠረው ይህ አጥቂ ኒያ ሳላሚና ፋማጉስታ የተባለውን የሳይፕረስ ክለብ ከተቀላለቀ በኋላ የመጀመርያ ግቡን ነው ያስቆጠረው። ተጫዋቹ በ2017 አሳዳጊ ክለቡ ማካቢ ሃይፋን ከለቀቀ በኋላ ለሀፖል ቤር ሻቫ ፣ ጊንሲልበርጊ ፣ ሀፖል ቴል አቪቭ እና ለሳይፕረሱ ክለብ ኒያ ሳላሚና ፋማጊስታ ተጫውቷል።

\"\"