ትላንት በዝናብ ተቋርጦ ዛሬ በሁለተኛው አጋማሽ የቀጠለው የወላይታ ድቻ እና ሲዳማ ቡና ጨዋታ 0-0 ተቋጭቷል።
ሲዳማ ቡና በፋሲሉ ድላቸው የተጠቀሙትን ቋሚ አሰላለፍ ቅያሪን ሳያደርጉ ለጨዋታው ሲቀርቡ ከቅዱስ ጊዮርጊሱ ሽንፈት አንፃር ወላይታ ድቻዎች ቅጣት ባሰሰተናገደው ያሬድ ዳዊት ምትክ አናጋው ባደግን ተክተው ጀምረዋል።
የቡድኖቹ ጨዋታ ከጀመረ ከአምስት ደቂቃዎች በኋላ በጣለው ከባድ ዝናብ የተነሳ ሁለቱም ቡድኖች ለመጫወት የፈለጉትን የጨዋታ መንገድ እንዳንመለከት ሜዳው ውሀ በመቋጠሩ ኳስን ለማንሸራሸር አመቺ ባለመሆኑ የጉሉ እንቅስቃሴዎችን ለማስተዋል አልታደልንም ይሁን እንጂ የተመጣጠነ ፉክክርን ነገር ግን የወላይታ ድቻ በንፅፅር ተሽለው መታየት በቻሉበት ቀዳሚው አጋማሽ ገና ጨዋታው በጀመረ በ1ኛው ደቂቃ ላይ ቢኒያም ፍቅሬ የሰጠውን ኳስ አበባየው አጂሶ ከርቀት መቶ ፊሊፕ ኦቮኖ አድኖበታል። የሜዳውን አለመመቸት የተገነዘቡ የሚመስሉ ሁለቱ ቡድኖች ወደ ተሻጋሪ ኳስ የጨዋታ መንገዳቸውን ለውጠዋል።
በሲዳማ በኩል 11ኛው ደቂቃ አጃህ ከርቀት መትቶ ቢኒያም የመለሰበት ከሁለት ደቂቃ መልስ ይገዙ ያመከናት ተጠቃሿ ነች። ወላይታ ድቻ ለማጥቃት የሚሄደበት መንገድ በገዘፈበት በአጋማሹ ድቻዎች ዘላለም አባተ ከቅጣት አሻምቶ መልካሙ በግንባር ሲጨርፋት ደጉ ደበበ ነፃ ቦታ ሆኖ የመታትን ኳስ ፊሊፕ ኦቮኖ አውጥቷታል። ሲዳማዎች ፍሬው ከርቀት ሞክሮ ቢኒያም ካወጣበት በኋላ ጨዋታው ያለ ጎል ወደ መልበሻ ክፍል አምርቷል። በጣለው ከባድ ዝናብ የተነሳ ሜዳው ለጨዋታ ምቹ ባለ መሆኑ የዕለቱ ዳኞች ሁለተኛው አጋማሽ በይደር ሊቆይ ችሏል።
ከዕረፍት መልስ የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ቀሪው 45 ደቂቃ ዛሬ ቀትር 7 ሲል ቀጥሏል። ወላይታ ድቻዎች በአጋማሹ የመጀመሪያዎቹን ሀያ ደቂቃዎች ኳስን በመቆጣጠር ወደ ተጋጣሚያቸው የሜዳ ክልል በተለይ የመስመር አጥቂዎቻቸው በመጠቀም በድግግሞሽ መድረስ ቢችሉም የሚያገኟቸውን አጋጣሚዎች ከጎል ጋር ለማስታረቅ የስልነት ችግሮች ነበረባቸው። በአንፃሩ ደቂቃው ሰባዎቹን ከተሻገረ በኋላ ጥሩ ወደ መሆን መጥተዋል ነገር ግን ቡድኑ ላይ ልክ ወላይታ ድቻዎች እንደነበረባቸው ደካማ አጨራረስ ይታይባቸው ስለ ነበር በረጃጅም ኳስ ይጫወቱ እንጂ በቀላሉ ኳስን ከመረብ ማገናኘት አልቻሉም።
አበባየው ከቅጣት አሻምቶ ደስታ ደሙ በግንባር የገጫትን እና መሐሪ በተመሳሳይ ከቅጣት ሲያሻማ አማኑኤል እንዳለ ወደ ውጪ የሰደዳት በተለየ መልኩ 75ኛው ደቂቃ አበባየው ዮሐንስ ከቅጣት አሻምቶ የድቻ ተከላካዮች ዝንጉነት ቢታከልበትም ቢኒያም ገነቱ በሚገርም ብቃት ኳሷን ወደ ውጪ አውጥቷል። በብዙ ረገድ ተዳክሞ የነበረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በመጨረሻም ያለ ጎል ተጠናቋል።