የአሰልጣኞች አስተያየት | ኢትዮጵያ መድን 0-2 ወልቂጤ ከተማ

\”የሜዳው ጭቃማነት እና የኛ የተቀዛቀዘ አቀራረብ ጨዋታውን ከባድ አድርጎብናል።\” – ምክትል አሰልጣኝ ለይኩን ታደሰ


\”በዚህ ዓይነት ብቃት ልንወርድ አይገባም። ያንንም ተጫዋቾቼ ያሳካሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።\” – አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ

ወልቂጤ ከተማ በጌታነህ ከበደ ግቦች ኢትዮጵያ መድንን 2-0 ከረታ በኋላ አሰልጣኝ የሚከተለውን አስተያየት ሰጥተዋል።

ምክትል አሰልጣኝ ለይኩን ታደሰ – ኢትዮጵያ መድን

ስለ ጨዋታው…

\”የሜዳው ጭቃማነት እና የኛ የተቀዛቀዘ አቀራረብ ጨዋታውን ከባድ አድርጎብናል።\”

ካለፉት ጨዋታዎች ተዳክመው ስለመቅረባቸው…

\”የመጀመሪያው ምክንያት ማንም ሰው እንደሚፈርደው ሜዳው ነው። ሜዳው እንደኛ ኳስ ይዞ ለመጫወት እና በደንብ ለማጥቃት ለሚፈልግ ቡድን አያግዝም ፤ እና ሜዳው አቀዛቅዞናል ብዬ አስባለሁ።\”

\"\"

በሀዋሳ እያደረጉት ስላለው ቆይታ…

\”ሀዋሳ ላይ ዛሬ አራተኛ ጨዋታችን ነው። የመጀመሪያውን ጨዋታ እኔ እንደ ጨዋታ አልቆጥረውም። ከዛ በኋላ ግን ከዛሬው ውጪ ጥሩ ነው።\”

አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ – ወልቂጤ ከተማ

ስለ ጨዋታው…

\”ጨዋታው እንደታየው በጣም ከባድ ነው። ለሁለት ነገር ነው ትግሉ አንደኛ መድን ጠንካራ ቡድን ነው ፤ ሁለተኛ ደግሞ ሜዳው ሌላ ትግል ይፈልጋል። እና በዚህ ከባድ ነገር ውስጥ ተጫዋቾቼ ድል በማሳካታቸው ደስተኛ ነኝ።\”

ቡድናቸው ውስጥ ስለታየው ከፍተኛ የመጫወት ፍላጎት…

\”ቡድናችን በየጊዜው ጥሩ ነው ፤ ብዙ አውርተናል። የነበረብን ድክመት የአጨራረስ ነበር እሱን ደግሞ ዛሬ አስተካክለናል። ባለፈውም እንዳልኩት ግብ ማግባት የስነልቦና ጉዳይ ነው። ጌታነህ ግብ ማግባት ስለሚያውቅ ነው ፤ እነ አቤል ወጣቶች ናቸው ብዙ ይስታሉ ግን ነገ ጥሩ ይሠራሉ ብዬ እጠብቃለሁ በየቀኑ መሻሻል እየታየባቸው ነው።\”

ስለ ወራጅነት ስጋት…

\”ላለመውረድ ነው እየሠራን ያለነው ፤ እርግጠኛም ነን። ምክንያቱም በዚህ ዓይነት ብቃት ልንወርድ አይገባም። ያንንም ተጫዋቾች ያሳካሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።\”

\"\"