የአሰልጣኞች አስተያየት | ሀዲያ ሆሳዕና 1-2 ኢትዮጵያ ቡና

\”በእንደዚህ ዓይነት ሜዳ እንደዚህ ዓይነት ጨዋታ ተጫውተህ ማሸነፍ ትልቅ ነገር ነው\” አሰልጣኝ ዮሴፍ ተስፋዬ

\”ጭቃው ትንሽ ከብዶን ነበር\” አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ

ኢትዮጵያ ቡና በአማኑኤል ዮሐንስ እና መስፍን ታፈሰ ግቦች ታግዞ ሀድያ ሆሳዕናን ባሸነፈበት እና ደረጃውን ካሻሸለበት ጨዋታ በኋላ የሁለቱም ቡድን አሰልጣኞች ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል።

\"\"

አሰልጣኝ ዮሴፍ ተስፋዬ

ስለ ጨዋታው…

ጨዋታው ጥሩ ነበር። አጀማመራችንም ጥሩ ነበር ፤ በመጨረሻም በድል አጠናቀናል።

በሁለተኛው አጋማሽ ስለታየው መቀዛቀዝ…

ውጤት ፍለጋ ነው ፤ ያለንበት ቦታ ውጥረት ነው። የሚመራ ቡድን በሁለተኛው አጋማሽ በዚህ መልኩ እንደሚመጣ ገምተን የጥንቃቄ ጨዋታ ነው የመረጥነው። እነሱ በተነሳሽነት ገቡ እኛም ውጤቱን ለማስጠበቅ ነው የገባነው። በእንደዚህ ዓይነት ሜዳ እንደዚህ ዓይነት ጨዋታ ተጫውተህ ማሸነፍ ትልቅ ነገር ነው።

\"\"

ስለ ብሩክ በየነ እንቅስቃሴ…

ብሩክ ዛሬ ከሌላው ግዜ በተሻለ በቡድን ሥራ ጥሩ እንቅስቃሴ ነው ያደረገው። እንደዚህ ዓይነት ተጫዋቾች መታገስ ግድ ነው። ኳስ ተበላሸበት ብለህ ወደ ውሳኔ አትገባም። ብሩክ አቅም እንዳለው እናውቃለን፤ እንጠብቀዋለን።

አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ

ስለ ጨዋታው…

በመጀመርያው አጋማሽ ተበልጠን ሁለት ግቦች ተቆጠሩብን ፤ በሁለተኛው አጋማሽ ግን አስተካክለን ገብተን ነበር ግን ያገኘናቸው የግብ ዕድሎች ስላልተጠቀምን አልተሳካም። ጭቃው ትንሽ ከብዶን ነበር። ግቦቹ ባልጠበቅናቸው ደቂቃዎች መግባታቸው ደግሞ አውርዶናል ፤ የመጀመርያው ግብ በሁለት ደቂቃ ነው የገባችው።

በሁለተኛው አጋማሽ ስለተደረጉ ቅያሬዎች…

መጀመርያ ላይ ባለፈው ጨዋታ ጥሩ እንቅስቃሴ አድርጎ ባህርዳርን ያሸነፈ ቡድን ስለነበር ለውጥ ሳናደርግ ነበር የገባነው። በሁለተኛው አጋማሽ ግን ለውጥ ማድረግ ግዴታ ስለነበር ፤ ጭቃም ስለነበር ጉልበት የሚያስፈልገው ብለን አስበን ነው ቅያሬዎች ያደረግነው።