ኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ማጣሪያ ተጋጣሚያዋን አውቃለች

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የኦሊምፒክ ማጣሪያ ጨዋታውን ከማን ጋር እና መቼ እንደሚያደርግ ተለይቷል።

\"\"

የ2024 ኦሊምፒክ ጨዋታዎች በፈረንሳይ ፓሪስ እንደሚደረግ ይታወቃል። በዚህም
ከደቂቃዎች በፊት በእግርኳስ በአፍሪካ ዞን አራት ዙሮች ያሉት የማጣርያ ጨዋታዎች ዕጣ የማውጣት ሥነ-ስርዓት ካይሮ ላይ ተካሂዷል። በዕጣው መሰረት የኢትዮጵያ ሴቶች እግርኳስ ብሔራዊ ቡድን ከቻድ አቻው ጋር የመጀመሪያ የደርሶ መልስ የማጣሪያ ጨዋታውን ከሐምሌ 3-11 ባሉት ቀናት እንደሚያከናውን ተረጋግጧል።

\"\"

የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች አሸናፊ ደግሞ ከናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ጋር በሁለተኛ ዙር ማጣሪያ እንደሚጫወት በቀጥታ ስርጭት በተላለፈው የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት ላይ ታውቋል።

\"\"