ኢትዮ ኤሌክትሪክ ለሦስተኛ ጊዜ አሰልጣኙን አሰናብቷል

ከሊጉ መውረዱን ያረጋገጠው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በዓመቱ ሦስተኛ አሰልጣኙን ሲያሰናብት ቀሪ ጨዋታዎችን በግብ ጠባቂ አሰልጣኙ ይመራል።

\"\"

በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ የገነነ ስምን የያዘው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ2011 ከፕሪምየር ሊጉ ከወረደ በኋላ ነበር በያዝነው ዓመት ዳግም መመለስ የቻለው። ክለቡ ከታችኛው የሊግ ዕርከን ካሳደገው አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና ጋር ለሰባት የሊግ ጨዋታዎች ከቆየ በኋላ በምትኩ ለረዳት አሰልጣኙ ገዛኸኝ ከተማ ኃላፊነት በመስጠት እስከ ሁለተኛው ዙር የመጀመሪያ ሳምንታት ድረስ ቢቆይም ለሁለተኛ ጊዜ በአሰልጣኙን በማሰናበት አሰልጣኝ ስምዖን አባይን በቦታው ሾሟል። እስከ 26ኛ ሳምንት ድረስ በአሰልጣኙ ሲመራ ቆይቶም በመጨረሻ አሰልጣኝ ስምዖንን ከኃላፊነት በማንሳት በምትካቸው የግብ ጠባቂ አሰልጣኙ ቅጣው ሙሉን ቀጣይ የመጨረሻ አራት ጨዋታዎችን እንዲመራ መሾሙን የክለቡ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሲሳይ ለማ ለሶከር ኢትዮጵያ አሳውቀዋል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሳምንታት በፊት ወደ አስር የሚደርሱ ተጫዋቾቹን የሆቴል ወጪ ለመቀነስ በማሰብ ማሰናበቱንም ሰምተናል።

\"\"