የአሰልጣኞች አስተያየት | ቅዱስ ጊዮርጊስ 2-1 ለገጣፎ ለገዳዲ

\”ከዚም በላይ ግቦች ማስቆጠር ነበረብን\” ዘሪሁን ሸንገታ

\”ውጤቱ ይገባቸዋል\” ዘማርያም ወልደግዮርጊስ

ዘርይሁን ሸንገታ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

ስለ ጨዋታው

ጨዋታው ጠንካራ ነበር። ቀድሞ የወረደ ቡድን አይመስልም ፤ ጥሩ እግርኳስ ነው የሚጫወቱት። ለህልውናቸው እና ለሞያቸው ጠንክረው ስለተጫወቱ ጨዋታው ጠንካራ ነበር። ከጨዋታው ቀድመንም ጠንካራ እንደሚሆን ገምቼ ነበር።
\"\"
በጨዋታው ስላሳዩት እንቅስቃሴ

በጨዋታው ብዙ ኳሶች አምክነናል፤ ከዚም በላይ ግቦች ማስቆጠር ነበረብን። ተጋጣምያችን ካስቆጠሩት ኳስ ውጭ ይህነው የሚባል ዕድል አልፈጠሩም። በተጨማሪም ቡድናችንም ብዙ የጎል ዕድሎች ፈጥሯል። በችኮሎ ዕድሎች አምክነናል። ከዛውጭ ግን ጥሩ ነበርን ፤ እርግጥ ነው የመጨረሻው ጎል መግባት አልነበረበትም። እንደ አጠቃላይ ጨዋታው ግን ጥሩ ነበር ፤ ሁሉም ቡድን እንደ ለገጣፎ ጠንካራና ሞያውን አክብሮ ቢጫወት ደስ ይለኛል።

ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ – ለገጣፎ ለገዳዲ

ስለ ጨዋታው

ጨዋታው ጥሩ ነበር ፤ ታክቲካሊ ጥሩ ነበርን። ግን የጥራት ችግር አለ ቡድናችን ላይ በዛ ነው የተሸነፍነው። እንደ ቡድን የተሻለ ነገር አድርገናል፤ ጊዮርጊስን ነው የገጠምነው። ውጤቱ ይገባቸዋል ፤ ሰርተው ነው የመጡት። እንኳን ደስ አላቹህ ማለት እፈልጋለሁ።
\"\"
ቡድኑ ስላሳየው የተሻለ እንቅስቃሴ

ስነ-ልቦናው ነው የሚመስለኝ እንጂ ለዚህ ጨዋታ በሚገባ ሰርተን ተዘጋጅተን ነበር የመጣነው። ግን በግል የተወሰኑ ተጫዋቾች ጥሩ አልነበሩም ፤ በዚህ ምክንያት የተሻለ እንዳንንቀሳቀስ ሆነናል። እንደአጠቃላይ ግን ጨዋታው ጥሩ ነበር።