መቐለ 70 እንደርታ በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ ሰጥቷል

የ2011 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፕዮኖቹ ምዓም አናብስት በወቅታዊ ሁኔታ ውይይት አድርገው መግለጫ ሰጥተዋል።

የክለቡ የበላይ ጠባቂ አቶ ይትባረክ አምሀ፤ ስራ አስከያጁ አቶ ሽፈራው ተክለሃይማኖት እና የክለቡ ፕሬዝዳንት አቶ ይርጋ ገብረእግዚአብሔር በጋራ በሰጡት መግለጫ ስለ ክለቡ አሁናዊ ሁኔታ እና ቀጣይ እርምጃዎች የተመለከተ ሰፊ ማብራርያ ተሰጥቶበታል። የቦርድ አባላት እና የተወሰኑ የክለቡ ደጋፊዎች በተገኙበት ውይይት የተነሱ አንኳር ነጥቦች እንደሚከተለው አዘጋጅተነዋል።

\"\"

የክለቡ ስራ አስከያጅ አቶ ይርጋ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የተከፈተው መድረክ ላይ በቅድምያ ሀሳባቸው የሰጡት ከከተማ መስተዳድሩ ተወክለው የመጡት አቶ ይትባረክ አምሀ መስተዳድራቸው ክለቡን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል።
በገለፃቸውም \”ቀደም ብለን በስፖርት እና ተመሳሳይ ዘርፎች ላይ ጥናት አድርገን እንቅስቃሴዎች መጀመር እንዳለባቸው ወስነናል። መቐለ 70 እንደርታ በምን መንገድ ይመለስ ለሚለው ጥያቄም ሰፊ ውይይት አድርገናል፤ በዚህም በጣም ደስተኞች ነን። በዛ መሰረት አስተዳደራችን ማድረግ ያለበትን ነገር እንዲያደርግ ክለቡ ደግሞ የራሱን ድርሻ ወስዶ እንዲሰራ ወስነናል\”ብለዋል።

ቀጥለው ሀሳባቸው የሰጡት አቶ ይርጋም ክለቡ ባለቤትነቱ የህዝቡ እና የመስተዳድሩ መሆኑን ገልፀው መስተዳድሩ ክለቡን ለመደገፍ ያሳየው ቁርጠኝነት አድንቀዋል። ፕሬዝዳንቱ ቀጥለውም \”የታሰበው ነገር እውን እንዲሆን ሌትቀን መስራት አለብን፤ በተለይም ስራውን እንድናስፈፅም አደራ የተሰጠን አካላት። ክለባችን ልዩ የሚያደርገው የእግር ኳስ ክለብ ብቻ አደለም፤ ክለባችን በብዙ ዘርፍ ነው የሚሳተፈው። በእግርካስ በሁለቱም ፆታ፤ በብስክሌት እና በእጅ ኳስ። እንደዚ አይነት ኃላፊነት ያለው ክለብ በሀገራችን የለም፤ ሸክማችን ብዙ ነው\” ካሉ በኋላ ለዚህ የሚመጥን ስራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል።


ፕሬዝዳንቱ ቀጥለውም \”ወደ ክልላዊ እና ሀገራዊ ውድድሮች እንድንመለስ የተለያዩ ጥያቄዎች እየቀረቡ ነው። ለዚህ መሳካት ደግሞ የረዥም እና አጭር ጊዜ እቅድ አውጥተን እናፀድቃለን\” ብለዋል።

ቀጥለው ሀሳባቸው የሰጡት የክለቡ ስራ አስከያጅ አቶ ሽፈራውም የዛሬው መድረክ በዋናነት ስለክለቡ ወቅታዊ ሁኔታ የምክክር መድረክ መሆኑን ጠቅሰው ተከታዩን ሀሳብ ሰጥተዋል። \”የሀገር አቀፍ እግር ኳስ ፌደሬሽን የሚከታተል አንድ ግለሰብ አዲስ አበባ ላይ ወክለናል። ፕሬዝዳንታችንም ከሁለት ጊዜ በላይ ተመሳሳይ ተልእኮ ይዞ አዲስ አበባ ሄዷል። ጉዳዩ የቅርበት ክትትል ያስፈልገዋል\” ብለዋል።

ስራ አስከያጁ ቀጥለውም ስለ ክለቡ አሁናዊ ሁኔታ ተከታዩን ሀሳብ ሰጥተዋል \”ስለዚህ ጉዳይ ለደጋፊያችን መግለፅም ተገቢ ስለሆነ በእነሱ በኩል(ኢትዮጵያ እግር ፌዴሬችን) እንደ ፍላጎት በቃል ደረጃም ቢሆን የእኛ መመለስ ላይ አዎንታዊ ነገር አለ፤ በደብዳቤ ደረጃ ግን የደረሰን ነገር የለም። ሌላው ከከተማ አስተዳድር ጋር የተጀመሩ ውይይቶች አሉ፤ በቀጣይም ቅርፅ ይዘው ይቀጥላሉ። ባለፉት ስልሳ ዓመታት ሁኔታዎች በተቀየሩ ቁጥር የመቐለ ክለቦች ህልውና ጥያቄ ውስጥ ይገባል፤ ወድቀው ለመነሳት ረዥም ጊዜ ፈጅቶባቸዋል። አሁን እንደ ቀድሞው ረዥም ጊዜ መቆየት አደጋ ነው። በርግጥ ፈተናችን ሚዛኑ ከባድ ነው\”ብለዋል።

\"\"

ስራ አስከያጁ ስለ ቀጣይ ፈተናቸውም \”ዋና ፈተናችን ሀብት ማሰባሰብ ላይ ነው፤ ከዚህ በፊት የበጀታችን 25% ከሜዳ እና ከስፖንሰር ነበር። የተቀረው የከተማ አስተዳደር ነበር የሚሸፍነው። አሁን ግን ይሄ ስለማይገኝ ከባድ ነው። ይሄንን በምን መንገድ እንተካው የሚል ምክክር ያስፈልገዋል። ከሦስት የሚደርሱ ባለድርሻ አካላት የመጡ ሀሳቦች አሉ፤ በእነዚ ጉዳዮች ከቦርድ ጋር እንወያይበታለን። የመቀጠላችን እና ያለመቀጠላችን የሚወስነው የሀገራዊ ፌደሬሽን ውሳኔ እና ያለን የፋይናንስ ጉዳይ ነው\” ብለው ሀሳባቸው አገባደዋል።