የሊጉ የቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት የሚመለስበት ቀን ታውቋል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የምስል መብት ባለቤት የሆነው ሱፐር ስፖርት የቀጥታ ስርጭት ለማስተላለፍ የሚመለስበት ጊዜ ታውቋል።
\"\"

ከ2013 ጀምሮ የሀገራችንን ከፍተኛ የሊግ እርከን ውድድር በቀጥታ እያስተላለፈ የሚገኘው ሱፐር ስፖርት ዘንድሮ ከ24ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች በኋላ ጨዋታዎች እያሳየ እንደማይገኝ ይታወቃል። የሊጉ ውድድር በ28ኛ ሳምንት በአዳማ ከተማ አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ሲቀጥል የመጨረሻ 29ኛ እና 30ኛ ሳምንት ጨዋታዎችን ለማስተላለፍ ቀድሞ አቅዶ የነበረው ሱፐር ስፖርት አንድ ሳምንት በመጨመር ከ28ኛ ሳምንት ጀምሮ ውድድሩን ለማስተላለፍ እንደወሰነ ታውቋል።
\"\"
የሱፐር ስፖርት የፕሮዳክሽን ባለሙያዎች እና ጋዜጠኞች ከነገ በስትያ ረቡዕ አዳማ እንደሚገቡ ያወቅን ሲሆን ከሀሙስ ጀምሮ ያሉትን የ28ኛ ሳምንት ጨዋታዎችን እና ቅዳሜ የሚደረገውን ተጠባቂው የ26ኛ ሳምንት የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ባህር ዳር ከተማ ተስተካካይ መርሐ-ግብርም እንደሚያስተላልፍ ተረጋግጧል።