ሲዳማ ቡና እና መቻል ቅጣት ተላልፎባቸዋል

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራር እና ሥነ-ስርዓት ኮሚቴ በ27ኛ ሳምንት የታዩ የዲሲፕሊን ግድፈቶች ላይ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
\"\"
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራር እና ሥነ-ስርዓት ኮሚቴ የ27ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በተመለከተ ከትናንት በስትያ ባደረገው ስብሰባ ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሪፖርቶች ከመረመረ በኋላ ውጤት በማፅደቅ የተለያዩ ውሳኔዎችን ሰጥቷል። በክለቦች ደረጃ በታዩ ሪፖርቶችም በሁለት ክለቦች ላይ ከፍ ያለ የገንዘብ ቅጣቶች መተላለፋቸው ተገልጿል።
\"\"
ሲዳማ ቡና በሳምንቱ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የእለቱን ዳኛ አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት በመቅረቡ የክለቡ ደጋፊዎች በዕለቱ ለፈፀሙት ጥፋት ክለቡ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 50 ሺህ ብር እንዲከፍል ተወስኗል። ከሲዳማ ውጪ መቻል ከባህር ዳር ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ አንድ የክለቡ ደጋፊ ተመልካችን በቦክስ ስለመማታቱና ሁከት ስለማስነሳቱ ሪፖርት የቀረበበት በመሆኑ የክለቡ ደጋፊ በዕለቱ ለፈፀመው ጥፋት ክለቡ(መቻል) በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 25 ሺህ ብር እንዲከፍል ተወስኗል።