ለሉሲዎቹ የተጫዋቾች ጥሪ ተላልፏል

ለ2024 የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ለማለፍ የመጀመሪያ ዙር የማጣሪያ መርሐ-ግብር ያለባቸው የሉሲዎቹ አሠልጣኝ ፍሬው ለ34 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል።
\"\"
የ2024 የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የሴቶች እግርኳስ የአፍሪካ ዞን የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ድልድል ከቀናት በፊት መውጣቱ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በመጀመሪያው ዙር ማጣሪያ ከቻድ አቻው ጋር የተደለደለ ሲሆን የቡድኑ አሠልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤልም ለዚህ ጨዋታ 34 ተጫዋቾችን መርጠዋል። ተጫዋቾቹ ከነገ በስትያ ማክሰኞ በመዲናችን ተሰባስበው ዝግጅታቸውን እንደሚጀምሩም ተመላክቷል።

ግብ ጠባቂዎች

ፍሬወይኒ ገብሩ (ሀዋሳ ከተማ)
ፅዮን ግርማ (ሲዳማ ቡና)
ታሪኳ በርገና (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ቤተልሔም ዮሐንስ (አርባምንጭ ከተማ)

ተከላካዮች

ቤተልሔም በቀለ (መቻል)
ነፃነት ፀጋዬ (መቻል)
ቅድስት ዘለቀ (ሀዋሳ ከተማ)
መንደሪን ክንድይሁን (ሀዋሳ ከተማ)
ደመቀች ዳንኤል (አዳማ ከተማ)
ትዕግሥት ኃይሌ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)
ብዙአየሁ አበራ (ሀምበሪቾ ዱራሜ)
ኤልሳቤት ታምሩ (ሀንበሪቾ ዱራሜ)
ብዙአየሁ ታደሠ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ናርዶስ ጌትነት (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ድርሻዬ መንዛ (አርባምንጭ ከተማ)
\"\"

አማካዮች

ሣራ ኪዶ (መቻል)
መዓድን ሳህሉ (መቻል)
ፅዮን ፈየራ (አዳማ ከተማ)
ህይወት ደንጊሶ (ኢትዮ ኤሌክክሪክ)
ንግስት ኃይሉ (አዲስ አበባ ከተማ)
ራኬብ አለማየሁ (ኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ)
መሳይ ተመስገን (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ንቦኝ የን (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ንጋት ጌታቸው (ልደታ ክ/ከተማ)

አጥቂዎች

ሴናፍ ዋቁማ (መቻል)
ረድኤት አስረሳኸኝ (ሀዋሳ ከተማ)
ቱሪስት ለማ (ሀዋሳ ከተማ)
ማርታ ወልዴ (ሱሉልታ ከተማ)
ሎዛ አበራ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
አረጋሽ ካልሳ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
አርያት ኦዶንግ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ዓለሚቱ ድሪባ (ልደታ ክ/ከተማ)
ንግስት በቀለ (ቦሌ ክ/ከተማ)
በሬዱ በቀለ (ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ)