ኢትዮጵያ ቡና ዳግም ፊቱን ወደ ውጭ ሀገር አሠልጣኝ አዙሯል

የዘንድሮ የውድድር ዓመት እንደ ዕቅዳቸው ያልሆነላቸው ኢትዮጵያ ቡናዎች የውጭ ሀገር ዜግነት ያለው አሰልጣኝ ለመቅጠር ከጫፍ መድረሳቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
\"\"
ኢትዮጵያ ቡና ከወትሮ ጊዜ በተለየ የሊጉን ዋንጫ ለማግኘት ለ2015 የውድድር ዘመን በርካታ ተጫዋቾችን በማስፈረም ወደ ውድድር ቢገባም በሚፈለገው ደረጃ ያሰበውን ማሳካት አልቻለም። ለቀጣይ ዓመት የደጋፊውንም ሆነ የክለቡ አመራሮችን የሚያስደስት ውጤት ለማግኘት የሀገር ውስጥ አሰልጣኝ ለመቅጠር እንቅስቃሴ ቢያደርግም ጥረቱ በተለያዮ ምክንያቶች ስኬታማ መሆን አልቻለም። በዚህም መነሻነት የሀገር ውስጥ አሰልጣኝ ምልመላውን በማቋረጥ ፊቱን ወደ ውጭ ሀገር አሰልጣኝ ማዞሩን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
\"\"
በዚህም መሠረት የክለቡ ስራ አመራር ቦርድ ወደ አራት የሚጠጉ አሠልጣኞችን እየተመለከተ ሲሆን ከአራቱ ክሮሺያዊ አሠልጣኝ የተሻለ ዕድል እንዳላቸው ሰምተናል። ከአራቱ አሠልጣኞች ክሮዋቱ አሠልጣኝ ላይ ፍላጎቶች ያሉ ቢሆንም ከሰሞኑን የክለቡ ቀጣይ አሠልጣኝ ማን ይሆናል የሚለው ጉዳይ ቁርጥ ያለው ውሳኔ እንደሚሰጥበት ይጠበቃል።