የሴቶች ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ነገ ይጀመራል

የሦስተኛ ዓመት ውድድሩን ዘንድሮ የሚያደርገው የሴቶች ክልል ክለቦች ሻምፒዮና በነገው ዕለት ከመጀመሩ አስቀድሞ የዕጣ ማውጣት መርሐ-ግብር በዛሬው ዕለት ተከናውኗል።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አወዳዳሪነት በየዓመቱ የሚከናወነው የሴቶች ክልል ክለቦች ሻምፒዮና በዘጠኝ ክለቦች መካከል ከነገ ሰኔ 15 ጀምሮ በሀዋሳ ከተማ አስተናጋጅነት መደረግ ይጀምራል። ውድድሩ በነገው ዕለት በይፋ ከመጀመሩ አስቀድሞ ክለቦች በዛሬው የዕጣ ማውጣት መርሀግብራቸውን ፈፅመዋል።
\"\"
በእጣ አወጣጥ ስነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን የውድድር ዳይሬክተር አቶ ከበደ ወርቁ ፣ ወይዘሪት ምህረት ጉታ የፌዴሬሽኑ የሴቶች ልማት ባለሙያ ፣ አቶ አንበሴ አበበ የሲዳማ ክልል እግር ኳስ ፌድሬሽን ፕሬዝዳንት እና ማህሌት አስራት የዳኞች ኮሚቴ ተወካይን ጨምሮ የክለብ ተወካዮች ተገኝተዋል።

በሴንትራል ሀዋሳ ሆቴል 10፡00 ሰዓት ሲል መደረግ የጀመረው ክንውኑ ዘጠኝ ክለቦች ተሳታፊ እንደሚሆኑ የተጠቆመ ሲሆን በሁለት ምድብም ቡድኖቹ ተከፍለው ይወዳደራሉ። በድልድሉም

\"\"

ምድብ 1 – ቢሾፍቱ ከተማ ፣ ኤግልስ ዲላ ፣ አምቦ ጎል (ፊፋ) ፣ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ እና ደብረማርቆስ ከተማ ሲደለደሉ

ምድብ 2 – ሰሌክት ኮሌጅ ፣ ሲዳማ ፖይለት ፣ ገበዘ ማሪያም ከተማ እና ጉለሌ ክፍለ ከተማ ተካተዋል

ነገ ውድድሩ በሀዋሳ ሰው ሰራሽ ሜዳ ላይ በምድብ 1 በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ጅምሩን ሲያደርግ ጠዋት 3፡00 ቢሾፍቱ ከተማ ከ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከሰዓት 10፡00 ደግሞ ኤግልስ ዲላ ከ አምቦ ጎል ይጫወታሉ። በአጠቃላይ በውድድሩ አንደኛ እና ሁለተኛ ሆነው የሚፈፅሙ ቡድኖች በ2016 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ላይ እንደሚወዳደሩ ድረገፃችን በስፍራው ተገኝታ ለማወቅ ችላለች።
\"\"