ዋልያዎቹ ለዓለም ዋንጫ ማጣርያ የተመደቡበት ቋት ይፋ ሆነ

ከዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ድልድል በፊት ይፋ የሚሆነው የተሳታፊዎች ቋት ተገልጿል።

\"\"

ፊፋ አሜሪካ ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ለሚያዘጋጁት የ2026 የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ሐምሌ ላይ ከሚከውነው ምድብ ድልድል በፊት ሀገራት የሚገኙበት ቋት ይፋ አድርጓል። በዚህም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከስድስቱ ቋቶት ሱዳን፣ ሩዋንዳ፣ ብሩንዲ፣ ኮሞሮስ፣ ላይቤርያ፣ ቦትስዋና፣ ስዋቲኒ እና ኒጀር በተመደቡበት አምስተኛ ቋት ተመድቧል።

በሐምሌ 5 የምድብ ድልድሉ ይፋ ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ ቡድኖቹ በዘጠኝ ምድቦች ከተመደቡ በኋላ ምድባቸውን በአንደኝነት ያጠናቀቁ ዘጠኝ ሀገራት በቀጥታ ወደ ውድድሩ ሲያልፉ ምርጥ ሁለተኛ የሆኑ አራት ሀገራት በጥሎ ማለፍ ተጫውተው አሸናፊው አስረኛ ሆኖ ወደ ውድድሩ የሚያመራ ይሆናል።

\"\"