ዋልያዎቹ ቅዳሜ ከአልጄርያ ጋር ወሳኝ ፍልሚያ ያደርጋሉ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለኢኳቶርያል ጊኒው የ2015 የአፍሪካ ዋንጫ 4ኛ ምድብ ማጣርያ ጨዋታ ትላንት ምሽት ወደ አልጄርያ ተጉዟል፡፡ ቡድኑ ማሊን ከሜዳው ውጪ አሸንፎ የማለፍ ተስፋውን ነፍስ የዘራበት ሲሆን ተጋጣሚው አልጄርያ ደግሞ ያደረገቻቸውን ጨዋታዎች በሙሉ አሸንፋ ከወዲሁ ለአፍሪካ ዋንጫው ማለፏን አረጋግጣለች፡፡
አሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶ 21 ተጫዋቾችን ለአልጄርያው ጨዋታ የመረጡ ሲሆን ጌታነህ ከበደ በጉዳት ፣ ሳላዲን ሰኢድ በጉዳት እንዲሁም አሚን አስካር የፊፋ ፕሮሰስ ባለመጠናቀቁ ከአልጄርያ ጋር ለሚደረገው ጨዋታ አይሰለፉም፡፡
ዋልያዎቹ ባለፈው እሁድ ከዩጋንዳ ብሄራዊ ቡድን ጋር ባደረጉት የዝግጅት ጨዋታ 3-0 መረታታቸው ይታወሳል፡፡

ያጋሩ