ረጅሙ ተከላካይ የንግድ ባንክ አዲሱ ተጫዋች ለመሆን ተቃርቧል

በከፍተኛ ሊጉ ከሀምበሪቾ ዱራሜ ጋር ስድስት የውድድር ዓመታትን ያሳለፈው ቁመታሙ ተከላካይ ቀጣይ መዳረሻው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲሆን ስምምነት ፈፅሟል።
\"\"
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት መከፈትን ተከትሎ ኪቲካ ጀማን ከመድን የመጀመሪያ ፈራሚው አድርጎ በእጁ ያስገባው አዲስ አዳጊው ክለብ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሌላኛው አዲስ አዳጊ ክለብ ሀምበሪቾ ዱራሜ ረጅሙን የመሐል ተከላካይ እንዳለ ዮሐንስን ሁለተኛ ፈራሚው ለማድረግ ከጫፍ ደርሷል።
\"\"
እግር ኳስን ከምህንድስና ሙያው ጎን ለጎን በመጫወት በትውልድ ሀገሩ ክለብ በሆነው ሀምበሪቾ ዱራሜ ለስድስት የውድድር ዘመናት በአምበልነት እና በመሐል ተከላካይነት ሲጫወት የቆየው እንዳለ ዮሐንስ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሐ ክለቡ ሀምበሪቾን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ካሳደጉ ሁነኛ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ሆኖ ካጠናቀቀ በኋላ ቀጣዩ መዳረሻው ሌላኛው አዳጊው ክለብ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሆኑን ዝግጅት ክፍላችን አውቃለች።