‹‹ ቅዱስ ጊዮርጊስ ማርያኖ ባሬቶን ሊከስ መሆኑ ተሰማ ››

የሃገራችን የህትመት ውጤቶች ዛሬ ማለዳ ለህትመት ያበቋቸው የኢትዮጵያ እግርኳስን የሚመለከቱ ጉዳዮችን እንዲህ አጠናቅረናቸዋል፡፡

ሪፖርተር

ሪፖርተር በዛሬው እትሙ የጀርባ ገፅ ቅዱስ ጊዮርጊስ በብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶ ላይ ክስ ሊመሰርት እንደሚችል የሚያትት ዘገባ ይዞ ወጥቷል፡፡ አሰልጣኙ በሁለተኛው ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀዋሳ ከነማን ያስተናገደበትን ጨዋታ በስታድየም ተገኝነተው የተከታተሉ ሲሆን አይዛክ ኢሴንዴ በታፈሰ ተስፋዬ ላይ የሰራው ጥፋት ቀይ ካርድ ሊያሰጥ ይገባል በሚል በዳኞች ስራ ጣልቃ በመግባታቸው ቅዱስ ጊዮርጊስ ክስ ሊመሰርት እንደተዘጋጀ መሰማቱን ጋዜጣው ታማኝ ምንጪቼ አረጋግጠውልኛል ብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ስታድየምን ለግማሽ ክፍለ ዘመን በሳር ተንከባካቢነት ያገለገሉት አቶ ተ/ማርያም አደሮን ህልፈት ተከትሎ ‹‹ የካንቦሎጆ ተንከባካቢው ተ/ማርያም አደሮ (1916-2007) ›› በሚል ርእስ ስር አስቧቸዋል፡፡

ሪፖርተር በተጨማሪም በብሄራዊ ቡድኑ የዩጋንዳ ሽንፈት እና ቀጣይ ጨዋታ ዙርያ ፅሁፎች ይዞ ወጥቷል፡፡

 

 

ሊግ ስፖርት

‹‹ ሆሳም ሃሰን እየሰጠኝ ያለው ማበረታታት ጥሩ ደረጃ እንደሚያደርሰኝ አምናለሁ፡፡ ›› ኡመድ ኡኩሪ

የኢትሃድ አሌሳንድሪያው አጥቂ ስለ አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ ሆሳም ሃሰን ፣ ስለ ብሄራዊ ቡድኑ እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

‹‹ በተጫዋቾቼ ብቃት ኮርቻለሁ ›› ግርማ ሃ/ዮሃንስ

ባለፈው እሁድ በንግድ ባንክ 2-0 ከመመራት ተነስተው አቻ ስለወጡበት ጨዋታ የሙገሩ አሰልጣኝ ግርማ ሃ/ዮሃንስ አስተያየታቸውን ለሊግ ስፖርት ሰጥተዋል፡፡ አሰልጣኙ ስለ ጨዋታው ፣ስለ ተጫዋቾች እና የታክቲክ ለውጥም አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

ሰንደቅ

ሰንደቅ በጀርባ ገፁ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከአልጄርያ ጋር ስለሚያደርገው ጨዋታ ሰፋ ያለ ፅሁፍ ይዞ ወጥቷል፡፡

ባለፈው እሁድ ከዚህ አለም በሞት የተለዩት የአዲስ አበባ ስታድየም የሳር ተንከባካቢ አቶ ተ/ማርያም አደሮን አጭር የህይወት ታሪክ ይዞ ወጥቷል፡፡

ያጋሩ