ኢትዮጵያ መድን አዲስ ግብ ጠባቂ ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል

ከሌሎቹ የሊጉ ክለቦች በተሻለ በዝውውሩ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው መድን ግብ ጠባቂ አስፈርሟል።
\"\"
እስካሁን የአራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ያጠናቀቀው ኢትዮጵያ መድን አሁንም ሌሎች ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ ለማምጣት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። በዚህም በግብ ጠባቂ ቦታ አዲስ ተጫዋች ማምጣቱን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
\"\"
የክለቡ አምስተኛ ፈራሚ የሆነው ግብ ጠባቂው ተመስገን ዮሐንስ ነው። ያለፉትን ሁለት ተከታታይ ዓመታት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ሻምፒዮን መሆን የቻለው ተመስገን ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ቡድን እንዲሁም የክለቡ ተስፋ ቡድን ድረስ መጫወት ችሎ ነበር። ተጫዋቹ ያለፉትን አራት ዓመታት ወደ ዋናው ቡድን አድጎ የነበረ ቢሆንም በወጥነት መጫወት ግን ሳይችል መቅረቱ ይታወቃል።