ሲዳማ ቡና አንድ ተጫዋች ሲያስፈርም የሁለት ተጫዋቾችን ውል አድሷል

በዝውውር መስኮቱ ላይ ዘግየት ብሎም ቢሆን እየተሳተፈ የሚገኘው ሲዳማ ቡና አንድ ተጫዋች ሲያስፈርም የሁለት ተጫዋቾችን ውል አድሷል።
\"\"
የፕሪምየር ሊጉ ክለብ ሲዳማ ቡና ከደስታ ዮሐንስ ቀጥሎ አንድ አዲስ ተጫዋች ሲያስፈርም ከጊት ጋትኩት በመቀጠል  የሁለት ነባሮችን ውልም አድሷል።

ብርሀኑ በቀለ የክለቡ አዲሰ ፈራሚ ሆኗል። የቀድሞው የደቡብ ፓሊስ ፣ ሀዋሳ ከተማ እና ያለፈትን ሁለት የውድድር ዘመናት በሀድያ ያሳለፈው የመስመር ተከላካዩ በሁለት ዓመት ውል ሲዳማ ቡናን ተቀላቅሏል።
\"\"
በክለቡ ውል ካራዘሙ ተጫዋቾች መካከል የቀድሞው የወላይታ ድቻ ፣ ሀዋሳ ከተማ ፣ ሀምበሪቾ ዱራሜ ፣ አዳማ ከተማ እና በሲዳማ ቡና ያለፉትን ሁለት ዓመታት እየተጫወተ የነበረው ግብ ጠባቂው መክብብ ደገፉ እና ከወጣት ቡድኑ ያደገው የመስመር ተከላካዩ ደግፌ አለሙ በክለቡ ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ውል አራዝመዋል።