ሴኔጋላዊው የግብ ዘብ ቀጣይ ማረፊያው የጣና ሞገዶቹ ሊሆን ከጫፍ ደርሷል

ቁመታሙ ግብ ጠባቂ የባህርዳር ከተማ አዲሱ ተጫዋች ለመሆን እጅጉን ተቃርቧል።
\"\"
ከፕሪምየር ሊጉ ጎን ለጎን ኢትዮጵያን ወክለው በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ላይ የሚሳተፉት ባህርዳር ከተማዎች በዝውውር መስኮቱ በንቃት እየተሳተፉ ሲሆን ከአይቮሪያኑ ግብ ጠባቂ ታፔ አልዛየር እና ኢትዮጵያዊው ፋሲል ገብረሚካኤል ጋር መለያየታቸውን ተከትሎ በቦታው አላዛር ማርቆስን ማስፈረማቸው ይታወሳል። አሁን ደግሞ ፊታቸውን ወደ ሴኔጋላዊው ፓፔ ሰይዶ ማዞራቸውን እና ሊያስፈርሙት እጅጉን ስለመቃረባቸው ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
\"\"
የዴንማርኩን ክለብ ጃመር ቡጌትን በመልቀቅ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ የተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በሀድያ ሆሳዕና በመጫወት ጥሩ የውድድር ዓመትን ያሳለፈው ይህ ግብ ጠባቂ ከባህር ዳሮች ጋር እያደረገ የሚገኘው ድርድር መስመር እየያዘ ሲሆን በቅርቡም በይፋ ፊርማውን ያኖራል ተብሎ ይጠበቃል።