የአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ ወላይታ ድቻ አማካይ ወደ ክለቡ ለመቀላቀል ስምምነት ፈፅሟል።
ያሬድ ገመቹን የክለባቸው አሠልጣኝ አድርገው ከሾሙ በኋላ የወሳኝ ተጫዋቻቸው ውል በማራዘም ጅምራቸውን ያደረጉት ወላይታ ድቻዎች ከባዬ ገዛኸኝ ፣ አብነት ደምሴ እና ፀጋዬ ብርሀኑ ቀጥለው አማካዩ አበባየሁ ዮሐንስን አራተኛ ፈራሚያቸው ለማድረግ ከጫፍ ደርሰዋል።
ከደቡብ ፓሊስ እግር ኳስን ከጀመረ በኋላ በስልጤ ወራቤ ፣ ሀድያ ሆሳዕና እና ወደ ቀድሞው ክለቡ ሲዳማ ቡና ተመልሶ የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን ያሳለፈው አማካዩ በደቡብ ፓሊስ ካሰለጠኑትን ያሬድ ገመቹ ጋር ዳግም ለመስራት ወደ ወላይታ ድቻ ለማምራት እጅጉን ተቃርቧል።
