በአሠልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የሚመራው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች ቡድን የአጥቂ መስመር ተጫዋች ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።
የ2015 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮኑ ንግድ ባንክ ከፊቱ ላለበት አህጉራዊ ውድድር እንዲሁም ለቀጣይ ዓመት ውድድር ቤተልሔም አስረሳኸኝ እና ትንቢት ሳሙኤልን ከኢትዮ ኤሌክትሪክ አስፈርሞ የነበረ ሲሆን ከደቂቃዎች በፊት ደግሞ ሴናፍ ዋቁማን የክረምቱ የዝውውር መስኮት ሦስተኛ ፈራሚው አድርጓል።
ከጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ የተገኘችው ሴናፍ በአዳማ ከተማ አራት ዓመታት በቀጣይም በመቻል ሦስት ዓመታት ግልጋሎት የሰጠች ሲሆን በሁሉም የዕድሜ እርከን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኖችም ተጫውታ አሳልፋለች። 2011 ላይ ኮከብ ተብላ የተመረጠችው ተጫዋቿም በቀጣይ ሁለት ዓመታት በንግድ ባንክ የእግርኳስ ህይወቷን ለመቀጠል ፊርማዋን ማኖሯን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።