በዝውውሩ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርሟል።
በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከከፍተኛ ሊግ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ያደገው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዝውውር መስኮቱ የነቃ የሳትፎ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ከደቂቃዎች በፊት የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር ማጠናቀቁን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
ቡድኑን የተቀላቀለው የመጀመሪያው ተጫዋች ፎዐድ ፈረጃ ነው። የቀድሞ የአዳማ ከተማ እና ሰበታ ከተማ ተጫዋች ያለፉትን ሁለት ዓመታት በባህር ዳር ያሳለፈ ሲሆን አሁን አዲስ አዳጊውን ንግድ ባንክ በሁለት ዓመት ውል ተቀላቅሏል።
ሁለተኛው ተጫዋች ደግሞ ፈቱዲን ጀማል ነው። የቀድሞ የሀላባ ከተማ፣ ወላይታ ድቻ፣ ሲዳማ ቡና እና ኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች እንደ ፎዐድ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በባህር ዳር ካሳለፈ በኋላ መዳረሻው ንግድ ባንክ ሆኗል።