ወላይታ ድቻ አማካይ አስፈርሟል

የጦና ንቦቹ አመሻሹን የአማካይ ስፍራ ተጫዋች በሁለት ዓመት ውል አስፈርመዋል።
\"\"
አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹን አዲሱ የክለቡ አለቃ ካደረጉ በኋላ የወሳኝ ተጫዋቾችን ውል በማራዘም በመቀጠል ባዬ ገዛኸኝ፣ አብነት ደምሴ እና ፀጋዬ ብርሃኑን ያስፈረሙት ወላይታ ድቻዎች አመሻሹን አራተኛ ፈራሚያቸው ብዙዓየው ሰይፉ ሆኗል።

\"\"እግር ኳስን በትውልድ ሀገሩ ሮቤ ከተማ ካደረገ በኋላ በመቀጠል በሀላባ ከተማ በ2014 ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ በፕሪምየር ሊጉ በአዲስ አበባ ከተማ እንዲሁም የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን በወልቂጤ ከተማ ካደረገ በኋላ ቀጣዩ መዳረሻው በሁለት ዓመት ውል ወላይታ ድቻ ሆኗል።