ሲዳማ ቡና የወሳኙን አጥቂ ውል አራዝሟል

በዝውውር መስኮቱ የነቃ ተሳትፎን እያደረገ የሚገኘው ሲዳማ ቡና የወሳኙን አጥቂ ውል አራዝሟል።

\"\"

በቀጣዩ የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ተጠናክሮ ለመቅረብ በአሰልጣኝ ስዩም ከበደ መሪነት የአዳዲስ ተጫዋቾች ዝውውር እየፈፀመ የሚገኘው እና ጎን ለጎን ደግሞ ውላቸው የተጠናቀቁ ተጫዋቾችን ኮንትራት እያራዘመ ያለው ሲዳማ ቡና የአጥቂው ይገዙ ቦጋለን ውል ለሁለት ተጨማሪ ዓመት በዛሬው ዕለት አድሷል።

\"\"


ከሲዳማ ቡና ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ ያለፉትን ስድስት ዓመታት በፕሪምየር ሊጉ ለክለቡ ግልጋሎት የሰጠው ተጫዋቹ በዛሬው ዕለት በክለቡ ለተጨማሪ ዓመት የሚያቆየውን ውል አኑሯል።