ድሬዳዋ ከተማ ሦስት ተጫዋቾችን አስፈርሟል

የአሰልጣኝ አስራት አባተ ድሬዳዋ ከተማ የሦስት ተጫዋቾችን ዝውውር ሲቋጭ የአንድ ተጫዋቾች ውል አድሷል።

በፕሪምየር ሊጉ የቀጣይ ዓመት ጉዞው በዝውውሩ በመሳተፍ ቡድኑን ለማጠናከር ከቀናት በፊት ተመስገን ደረሰ በእጁ ያስገባው ድሬዳዋ ከተማ ከደቂቃዎች በፊት የሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ሲፈፅም የአንድ ተጫዋች ኮንትራት አራዝሟል።
\"\"
አማካዩ ሔኖክ አንጃ ድሬዳዋን ተቀላቅሏል። የቀድሞው ቡታጅራ ከተማ ፣ አዲስ አበባ ከተማ ፣ ኢትዮጵያ መድን ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ ፣ ገላን ከተማ እና ያለፈውን ዓመት በኢትዮ ኤሌክትሪክ የተጫወተው አማካዩ ድሬዳዋን በይፋ ተቀላቅሏል።

ሁለተኛው ፈራሚ ቴዎድሮስ ሀሙ ነው። በመሐል ተከላካይነት በአዲስ አበባ ከተማ እና ወልቂጤ ከተማ ከዚህ ቀደም የተጫወተ ሲሆን ሌላኛው የድሬዳዋ አዲሱ ፈራሚ ተጫዋች ሆኗል።
\"\"
ሀምዲ ቶፊክ ወደ ቀድሞው ክለቡ ተመልሷል። በድሬዳዋ ከተማ ከዚህ ቀደም በግብ ጠባቂነት ያገለገው ተጫዋቹ በከፍተኛ ሊጉ ይርጋጨፌ ቡና 2015 አሳልፎ ወደ ቀደመ ክለቡ ተመልሷል።

ቡድኑ ከአዳዲስ ፈራሚዎቹ በተጨማሪ የአጥቂው ሙኧዲን ሙሳን ውል ለሁለት ተጨማሪ ዓመት አራዝሟል።