በተለያዩ ክለቦች ሲፈለግ የቆየው አጥቂው ጌታነህ ከበደ በመጨረሻም ማረፊያው ታውቋል።
የዘንድሮውን የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከፍተኛ ጎል አግቢነትን በ18 ጎል ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ ያጠናቀቀው ጌታነህ ከበደ ያለፉትን 25 ቀናት በአሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌስቲቫል ላይ በክብር እንግድነት መቆየቱ ይታወቃል። ከሰሞኑን ወደ ሀገር ቤት መመለሱን ያወቁ ተለያዩ ክለቦች ሲያነጋግሩት ቢቆይም በስተመጨረሻ ለሲዳማ ቡና መፈረሙ ተረጋግጧል።
የቀድሞ የደቡብ ፖሊስ፣ የደደቢት፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ወልቂጤ ከተማ እንዲሁም በፕሮፋሽናል የእግር ኳስ ህይወቱ የደቡብ አፍሪካዎቹን ቢድቬስት ዊትዝ እና ፕሪቶዮሪያ ዩኒቨርሲቲው እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አጥቂ ጌታነህ ከበደ ዘለግ ላሉ ሰአታት ከተደረገ ድርድር በኋል ለ2 ዓመት ሲዳማ ቡናን በይፋ ተቀላቅሏል፡፡