ቴዎድሮስ ታፈሰ ነብሮቹን በአንድ ዓመት ውል ተቀላቀለ።
ቀድም ብለው የሰመረ ሀፍታይን ውል ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ያደሱት ሀድያ ሆሳዕናዎች አሁን ደግሞ አማካዩን ቴድሮስ ታፈሰ አራተኛ ፈራሚ ሆኗል።
በመቻል ሰባት የውድድር ዓመታት ካሳለፈ በኋላ እናት ክለቡን ለቆ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በሲዳማ ቡና ያሳለፈው ይህ አማካይ በስተመጨረሻ ከቀድሞ አሰልጣኙ ጋር በድጋሜ ለመስራት ምርጫውን አድርጓል።
እስካሁን ድረስ በረከት ወልደዮሐንስ እና ምሕረትአብ ገብረህይወት አስፈርመው የቀድሞ አጥቅያቸው ዳዋ ሆቴሳ ለመመለስ ከስምምነት የደረሱት ነብሮቹ የዳግም ንጉሴ እና ሰመረ ሀፍታይን ውል ማራዘማቸው ይታወሳል።።