በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከኢትዮጵያ መድን ጋር ቆይታ የነበረው አማካኝ ተጫዋች በስምምነት ከክለቡ ጋር መለያየቱ ታውቋል።
ወደ ሊጉ ባደገበት አመት ጥሩ የውድድር አመት ያሳለፈው ኢትዮጵያ መድን ለከርሞ እራሱን ለማጠናከር ወደ ዝውውሩ በስፋት የገባ ሲሆን አሁን ደግሞ ከአማካይ ተጫዋቹ ሀብታሙ ሸዋለም ጋር በስምምነት መለያየቱ ታውቋል።
አመዛኙን ጨዋታ ለቡድኑ ግልጋሎት የሰጠው ሀብታሙ በቡድኑ የሚያቆየው የአንድ አመት ቀሪ ውል እያለው ነው በስምምነት ከክለቡ ጋር የተለያየው።