በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ የሚካፈለው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሁለት ተጫዋቾችን በማስፈረም የአዳዲሶቹን ቁጥር አስር አድርሷል።
በአሰልጣኝ መሠረት ማኔ የሚመራው እና ያለፉትን ሦስት ዓመታት በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ ጠንከር ያለ ተሳተፎን እያደረገ የሚገኘው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከቀናቶች በፊት የነባር ተጫዋቾችን ውል ሲያራዝም ስምንት የሚጠጉ አዳዲስ ተጫዋቾችን ያስፈረመ ሲሆን በዛሬው ዕለት ሁለት ተጨማሪ በማከል የአዳዲሶቹን ቁጥር አስር አድርሷል።
ፂዮን እስጢፋኖስ የክለቡ ዘጠነኛዋ ፈራሚ ተጫዋች ሆናለች። የቀድሞዋ የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ረዘም ላሉ ዓመታት ደግሞ በመቻል ቆይታ የነበራት ተከላካዩዋ ወደ ኤሌክትሪክ አምርታለች። አስረኛ ፈራሚ ሆና ወደ ኤሌክትሪክ ያመራችው አጥቂዋ ስራ ይርዳው ናት። የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ላለፉት ሁለት ዓመታት በመቻል ከተጫወተች በኋላ ቀጣዩ መዳረሻዋ ኤሌክትሪክ ሆኗል።