የድሬዳዋ ከተማው ግብ ጠባቂ ለአረጋውያን መርጃ ማዕከል ድጋፍ አድርጓል

ድሬዳዋ ከተማ እየተጫወተ የሚገኘው የግብ ዘቡ ዳንኤል ተሾመ በአዳማ ለሚገኝ የአረጋውያን መርጃ ማዕከል በዛሬው ዕለት የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ጊዜያቸውን በበጎ ተግባራት ከሚያሳልፉ ጥቂት ተጫዋቾች መካከል አንዱ በሀምበሪቾ ከተማ፣ አዳማ ከተማ፣ አዲስ አበባ ከተማ እና ከተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ጀምሮ በድሬዳዋ ከተማ እየተጫወተ የሚገኘው ግብ ጠባቂው ዳንኤል ተሾመ አንዱ ነው። ዳንኤል በተለያዩ ወቅቶች የበጎ ተግባራትን ሲፈፅም የምናየው ሲሆን በዛሬው ዕለትም ተመሳሳይ ድርጊትን በአዳማ ከተማ አድርጓል።

ዛሬ ረፋድ ላይ ተጫዋቹ ፈለገ አረጋዊያን መርጃ በሚባል ማዕከል በመገኘት የገንዘብ ስጦታን ያበረከተ ሲሆን በቀጣይም በመዓከሉ የሚያስፈልጉ ነገሮች ለማድረግ እና በሌሎች ማዕከላትም በመገኘት ድጋፍን እንደሚያደርግ የገለፀልን ሲሆን ሌሎች እግር ኳስ ተጫዋቾችም ባላቸው የዕረፍት ወቅት በበጎ ምግባር ላይ መሳተፍ እንደሚገባቸው ለሶከር ኢትዮጵያ ሀሳቡን ሰጥቷል።