ትውልደ ኢትዮጵያዊው የባቫርያኑ ክለብ ተጫዋች…

በጀርመኑ ታላቅ ክለብ ባየርን ሙዩኒክ የሚጫወተው ተስፋ የተጣለበት ተጫዋች ማነው?

በባቫርያኑ ክለብ አንድ ተስፈኛ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ተጫዋች አለ፤ ስሙም ልኡል ብሩክ ዓለሙ ይባላል። ትልቅ ተስፋ የተጣለበት የአጥቂ አማካይ ነው። የእግር ኳስ ሂወቱ በዋና ከተማዋ በርሊን በሚገኘው Hertha 03 Zehlendorf የተባለ ክለብ ጀመረ። በመቀጠልም Hertha BSC፣ FC Viktoria 1889 Berlin ከተጫወተ በኋላ በ2018 ታላቁን ባየር ሙዩኒክ ተቀላቅሎ በክለቡ አራት የዕድሜ እርከን ቡድኖች ተጫውቷል። በአሁኑ ሰዓት በሙዩኒክ ከአስራ ዘጠኝ ዓመት በታች ቡድን ውስጥ በመጫወት ላይ ሲገኝ በ2022 እስከ 2025 ከቡድኑ ጋር የሚያቆየው ውል ፈርሟል።

ባለፈው ዓመት ወርሀ ጥር torn cruciate ligament የተባለ አስከፊ ጉዳት ገጥሞት ለወራት ከሜዳ ለመራቅ የተገደደው ይህ የአስራ ስምንት ዓመት ተጫዋች ከቡድኑ ጋር የቅድመ ውድድር ዝግጅት አልጀመረም። ክለቡ በተጫዋቹ ጉዳት ዙርያ ያለው ነገር ባይኖርም ያጋጠመው ጉዳት ከስድስት እስከ ዘጠኝ ወራት ከሜዳ የሚያርቅ ጉዳት እንደመሆኑ በቅርቡ ወደ ሜዳ ሊመለስ እንደሚችል እንደሚችል ይገመታል።