የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን እየሰሩ የሚገኙት አዳማ ከተማዎች 11ኛ ተጫዋቻቸውን አስፈርመዋል።
በመቀመጫ ከተማቸው የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን እየሰሩ የሚገኙት አዳማ ከተማዎች በዝውውር ገበያው እስከ አሁን ተክለማርያም ሻንቆ ፣ መላኩ ኤልያስ ፣ ሱራፌል ዐወል ፣ ኤፍሬም ዘካርያስ ፣ ፍቅሩ አለማየሁ ፣ አህመድ ረሺድ ፣ ተስፋሁን ሲሳይ ፣ ሬድዋን ሸሪፍ ፣ አሸናፊ ኤልያስ እና አቡበከር ሻሚልን በይፋ ያስፈረሙ ሲሆን አሁን ደግሞ 11ኛ ፈራሚ በማድረግ አጥቂው ጫላ በንቲን የግላቸው አድርገዋል።
የቀድሞው የነቀምት ከተማ ፣ ሀምበሪቾ ዱራሜ ፣ ቡራዩ ከተማ እና ጅማ አባጅፋር አጥቂ የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን በድሬዳዋ ከተማ ካሳለፈ በኋላ ቀጣዩ መዳረሻው የአሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለው አዳማ ሆኗል።
