ቅዱስ ጊዮርጊስ ወጣቱን ግብ ጠባቂ አስፈርሟል

ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሙከራ ጊዜን እያሳለፈ የነበረው ግብ ጠባቂ በይፋ የሦስት ዓመት ውል ፈርሟል።

በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊ በመሆኑ ቀደም በማለት የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን ማድረግ የጀመረው ቅዱስ ጊዮርጊስ በዝውውር ገበያው እስከ አሁን ጥቂት ተሳትፎን ያደረገ ሲሆን አሁን ደግሞ የሙከራ ጊዜን ሰጥቶት የነበረው የግብ ዘቡ አዲሱ ቦቄን በሦስት ዓመት ውል በዛሬው ዕለት አስፈርሟል።

በከፍተኛ ሊጎቹ ክለቦች ኮልፌ ቀራኒዮ እና ያለፈውን ዓመት ደግሞ በባቱ ከተማ ሲጫወት ያሳለፈው ግብ ጠባቂ ለመጀመሪያ ጊዜ በፕሪምየር ሊጉ ለመጫወት ለፈረሰኞቹ ፊርማውን አኑሯል።