ላለፉት ሦስት ዓመታት ተቋርጦ የቆየው የትግራይ ዋንጫ ትናንት ተጀመረ።
ከጦርነቱ በኋላ የመጀመርያ የሆነው እና አስራ ሁለት ክለቦች የሚሳተፉበት የትግራይ ዋንጫ በትናንትናው ዕለት ጅማሮውን አድርጓል። የውድድሩ መክፈቻ በነበረው ጨዋታ ስሑል ሽረ ራያ አዘቦን ሁለት ለአንድ ስያሸንፉ ሁለተኛ የነበረው እና ማራኪ እንቅስቃሴ በታየበት ጨዋታ አክሱም ከተማ እና ፈራውን አቻ ተለያይተዋል።
ውድድሩ ዛሬ ሲቀጥል በምድብ ሁለት የሚገኙት መቐለ 70 እንደርታ እና ዋልታ ፖሊስ 7:00 ጨዋታቸው ሲያደርጉ፤ በ9:00 ደግሞ ደደቢት ከ ሓዉዜን ይጫወታሉ።
በዋነኝነት የክልሉ የእግር ኳስ እንቅስቃሴ ዳግም ለማነቃቃት አልሞ በሸቶ ሚድያ እና የትግራይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጋራ የተዘጋጀው ይህ ውድድር ደጋፊ ወደ ስቴድየም ገብቶ እንዲመለከተው የሸቶ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን ስራ አስከያጅ አቶ ግደይ አብርሀ ጥሪ አቅርበዋል።