በወዳጅነት ጨዋታ ኢትዮጵያ ነገ ዩጋንዳን ትገጥማለች

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 27 አባላትን ይዞ ወደ ካምፓላ አምርቷል፡፡ በነገው እለትም በናምቡሊ ስታድየም ከዩጋንዳ ብሄራዊ ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታውን ያደርጋል፡፡

ዋና አሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶ ኢንቴቤ አየር ማረፍያ ሲደርሱ ከካዎዎ ስፖርት ድረ-ገፅ በሰጡት አስተያየት ‹‹ ዩጋንዳ በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ ጠንካራ ሃገራት አንዷ ናት፡፡ ብሄራዊ ቡድኑን አከብራለሁ ፤ ነገር ግን እዚህ የመጣነው ጥሩ ነገር ለማሳየት ነው፡፡ .. ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አርብ ወደ ካንፓላ አምርቶ ኢምፔርያል ሮያል ሆቴል ያረፈ ሲሆን ከትላንት ምሽት ጀምሮ ልምምድ መስራት ጀምሯል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 27 አባላት እነዚህ ናቸው፡-

ግብ ጠባቂዎች

ጀማል ጣሰው

ታሪክ ጌትነት

ተከላካዮች

ብርሃኑ ቦጋለ

ቢያድግልኝ ኤልያስ

ዴቪድ በሻህ

ግርማ በቀለ

ሳላዲን በርጊቾ

ዋሊድ አታ

አማካዮች

ታደለ መንገሻ

ምንተስኖት አዳነ

ናትናኤል ዘለቀ

ጋቶች ፓኖም

ፋሲካ አስፋው

አንዳርጋቸው ይሳቅ

ሄኖክ ካሳሁን

ዩሱፍ ሳሌህ

ኤፍሬም አሻሞ

አጥቂዎች

ዳዋ ሁቴሳ

ራምኬ ሎክ

ፉአድ ኢብራሂም

ዳዊት ፍቃዱ

ስታፍ

ዋና አሰልጣኝ – ማርያኖ ባሬቶ

ረዳት አሰልጣኞች – ፋሲል ተካልኝ እና ዳንኤል ፀሃዬ

የቡድን መሪ – ቾውል ቤል

ህዝብ ግንኙነት – ወንድምኩን አላዩ

ማናጀር – በኃይሉ አበራ

ያጋሩ