የግብፅ የፀጥታ አካላት የቅዱስ ጊዮርጊስ እና አል አህሊን ጨዋታ በተመለከተ አዲስ ውሳኔ አስተላልፈዋል።
የግብፅ መንግሥት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና አል አህሊ የፊታችን እሁድ በሚያደርጉት የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የመጀመርያ ዙር ጨዋታ 30,000 ደጋፊዎችን ካይሮ ስታዲየም ገብተው እንዲመለከቱ ፍቃድ ሰጥቷል። አል አህሊዎች በድህረ ገፃቸው ይፋ ባደረጉት ይፋዊ መግለጫ ክለቡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ለሚኖረው ጨዋታ ወደ 30,000 የሚጠጉ ደጋፊዎች እንዲታደሙ ከፀጥታ አካላት ፍቃድ ማግኘታቸውን ገልፀዋል።
ከዚህ ቀደም በግብፅ በተደረጉ የሀገር ውስጥ የሊግ ጨዋታዎች እና የአፍሪካ ውድድሮች ወደ 10,000 የሚጠጉ ደጋፊዎች ስታዲየም እየተገኙ ጨዋታዎች ሲከታተሉ ቆይተዋል። አሁን የግብፅ የፀጥታ አካላት ውሳኔውን በመቀልበስ 30,000 ደጋፊ ስታድየም እንዲታደሙ ፈቅደዋል።
በተያያዘ ሌላ ዜና ደቡብ አፍሪካዊው የአል አህሊ ወሳኝ አጥቂ ፔርሲ ታው ከቀናት በፊት በገጠመው መጠነኛ ጉዳት ለጨዋታው የመድረሱ ጉዳይ አጠራጣሪ መሆኑ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ያመላክታሉ።