የአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌው ሀድያ ሆሳዕና የአማካይ ስፍራ ተጫዋች በአንድ ዓመት ውል አስፈርሟል።
የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመንን የፊታችን ቅዳሜ መቻል በመግጠም የሚጀምረው ሀድያ ሆሳዕና በክረምቱ ከአሰልጣኝ ቡድን አባላት ጀምሮ በተጫዋቾችም ረገድ በርከት ያሉ ዝውውሮችን መፈፀሙ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ አማካዩ ስንታየሁ ዋለጬን በአንድ ዓመት ውል የመጨረሻው የክለቡ ፈራሚ ተጫዋች አድርጎታል።
ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ ያለፉትን ሰባት ዓመታት ደግሞ በዋናው የኤሌክትሪክ ቡድን ውስጥ በከፍተኛ ሊጉ እና በፕሪምየር ሊጉ ላይ በመጫወት ካሳለፈ በኋላ በእግርኳስ ዘመኑ ሁለተኛ ወደ ክለብ ሆነው ሀድያ ሆሳዕና አምርቷል።