በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ የሚሳተፈው ቦሌ ክፍለ ከተማ የበርካታ ተጫዋቾችን ዝውውር ሲፈፅም የነባሮችን ውልም አድሷል።
በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ ጥሩ እግርኳስን በመጫወት የሚታወቀው ቦሌ ክፍለ ከተማ ለዘንድሮው የሊግ ተሳትፎው ራሱን አጠናክሮ ለመቅረብ ባጣቸው ተጫዋቾች ምትክ ሊሆኑ የሚችሉ አስራ ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾችን አሰልጣኝ ቻለው ለሜቻ ሲያስፈርሙ የነባር 10 ተጫዋቾችን ውልም አድሰዋል።
ክለቡን የተቀላቀሉ አዳዲስ ፈራሚዎች ግብ ጠባቂ ሮማን አምባዬ ከስፖርት አካዳሚ ፣ ተከላካዮች ፍቅርተ ገዛኸኝ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ቤተልሔም ስለሺ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ፅግነሽ አዴ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ አደራ አናጋው ከይርጋጨፌ ቡና ፣ ብዙነሽ ቡልቻ ከስፖርት አካዳሚ ፣ አማካዮች ብዙአየሁ ፀጋዬ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ሚሊየን ጋይም ከስፖርት አካዳሚ ፣ ራኬብ ሀብታሙ ከስፖርት አካዳሚ ፣ ቅድስት ዳኛቸው ከይርጋጨፌ ቡና ፣ አጥቂዎች ትግስት ወርቄ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እና ፍሬህይወት ተስፋዬ ከይርጋጨፌ ቡና ናቸው።
ውላቸውን ያደሱ ተጫዋቾች ሊንጎ ኡማን ፣ ትብቃ ፈንቴ ፣ ቃልኪዳን ሸዋነህ ፣ ሒሩት ብርሀኑ ፣ እቴነሽ ደስታ ፣ ሜላት አሊሙዝ ፣ ይዲዲያ አጫ ፣ ምርትነሽ ዮሀንስ ፣ ጤናዬ ለታሞ እና ሜላት ጌታቸው መሆናቸው ታውቋል።