ቡናማዎቹ ብርቱናማዎቹን 1-0 ከረቱበት ጨዋታ በኋላ ሁለቱ አሰልጣኞች ሀሳባቸውን ለሶከር ኢትዮጵያ አጋርተዋል።
አሰልጣኝ አስራት አባተ – ድሬዳዋ ከተማ
ስለ ጨዋታው…
“ጨዋታው ጥሩ የሚባል ጨዋታ ነው። ጠንካራ ፉክክር የተደረበት ነበር። በተለይ ከዕረፍት በፊት ያገኘናቸውን ዕድሎች መጠቀም አልቻልንም እንጂ ጥሩ እንቅስቃሴ አድርገናል። የገባብን ከጥንቃቄ ስህተት ከተጫዋቻችን ያመለጠ ኳስ እና በጊዜም ነበር። በተወሰነ መልከ ለመነሳሳት ቸግሮን ነበር። በኋላ ግን የተሻለ መንቀሳቀስ ችለናል። ጥሩ ፉክክር የነበረበት ጨዋታ ነው።”
በአጥቂ እና አማካዮች ላይ የነበረው የግንኙነት ድክመት…
“ደካማ ነበር ማለት አይቻልም። ምክንያቱም አጥቂው ወደ ጎሉ ጋር ሲደርስ ይታያል። አፈፃፀም ላይ ግን ትንሽ ክፍተት ነበረብን ያገኘነውን የመጨረስ ችግሮች በደንብ የታየበት ሁኔታ ነበር። እንደውም ከዕረፍት በፊት በተወሰነ መልኩ አጨዋወታቸውን በማየት ለመቆጣጠር ጥረት አድርገናል።”
ስለ ቅያሪ መዘግየት…
“ቅያሪ እንግዲህ የሚፈቅድልህ ሰዓቶች አለ። የጨዋታው እንቅስቃሴ የሚፈቅደው ሁኔታ አለ። ያንን ለመጠቀም ነው ቅያሪ ያደረግነው ፣ ቅያሪውን ትክክለኛ ሰዓት ላይ ነው ያደረግነው በዚህም ምክንያት ዕድሎችን ማግኘት ችለናል። ያንን ዕድል ያለ መጠቀም እንጂ ቅያሪው የዘገየ ቅያሪ አልነበረም”።
አሰልጣኝ ኒኮላ ካቫዞቪች – ኢትዮጵያ ቡና
ስለበድናቸው አቀራረብ እና ስለውጤቱ
“ደስተኛ መሆን እንዳለብን አስባለሁ። ምክንያቱም ስመጣ አምና ኢትዮጵያ ቡና ውብ እግርኳስ ቢጫወትም ውጤቱ እንደፈለገው አልሆነለትም። አሁን ግን የተለየ ቡድን ነው ያለን። በሁሉም የሜዳው ክፍል ላይ ከፍ ያለ ጫና ፈጥረን ቀጥተኛ እግርኳስ እየተጫወትን ነው። በዚህም ነጥቦችን ለማግኘት እየሞከርን ነው። ከዚህ ቀደም በአጨዋወት ምርጫዬ የተለየ ሀሳብ ነው የነበረኝ ፤ እዚህ ስመጣ ያንን ቀይሪያለሁ። ስለዚህ ዋናው ሦስት ነጥብ ማሳካት እና በሰንጠረዡ የላይኛው ክፍል ላይ መገኘት ነው።”
ስለተጋጣሚቸው አቀራረብ…
“ከአምስት ቀናት በፊት ጀምሮ ከ15-20 ደቂቃ የሚሆን የቪዲዮ ትንተና ሰርተናል። በዚህም የጨዋታ መንገዳቸውን ስለተረዳን አደጋ ሊፈጥሩ የሚችሉባቸውን ክፍተቶች ዘግተን ቀርበናል።”