አበባው የኢትዮጵያን የማለፍ ተስፋ ነፍስ ዘራበት

በ2015 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከሜዳው ውጪ ያልታጠበቀ ድል አስመዝግቦ የጨለመ የማለፍ ተስፋውን አለምልሟል፡፡

ማሊዎች ግብ በማስቆጠር ቅድሚያ የያዙት በ32ኛው ደቂቃ በባካሪ ሳኮ አማካኝነት ነበር፡፡ ብዙም ሳይቆይ በ36ኛው ደቂቃ ኡመድ ኡኩሪ ከጌታነህ ከበደ የተሸገረለትን ኳስ አስቆጥሮ ኢትዮጵያን አቻ አደረገ፡፡ የመጀመርያው ግማሽ የተጠናቀቀውም ጌታነህ ከበደ ኢትዮጵያን መሪ የምታደርግ ግብ አስቆጥሮ ነው፡፡

በሁለተኛው አጋማሽ ኢትዮጵያ መሪነቷን ለማስጠበቅ ማሊም ግብ ለማስቆጠር ከፍተኛ ትግል ያደረጉ ሲሆን በ62ኛው ደቂቃ ግብ በማስቆጠር እና ለኡመድ ግብ በማቀበል በጨዋታው ተፅእኖ ሲፈጥር ያመሸው ጌታነህ ከበደ በቀይ ካርድ ከሜዳ መውጣት እና ከ3 ደቂቃዎች በኋላ ሙስጣፋ ያትባሬ ነማሊን አቻ ማድረጉ የዋሊያዎቹን ምሽት ከባድ አድርጎበት ነበር፡፡

በመጨረሻም መደበኛው ሰአት ተጨናቆ በጭማሪው ሰአት የተገኘችውን ቅታት ምት አበባው በቀጥታ ወደ ጎልነት ቀይሯት የኢትዮጵያን የማለፍ ተስፋ ከሞተበት ቀስቅሷል፡፡

በሌላው የምድቡ ጨዋታ የአፍሪካዋ ቁጥር አንድ አልጄርያ ማላዊን በቀላሉ 3-0 አሸንፋ ለሞሮኮ የአፍሪካ ዋንጫ በማለፍ ቀዳሚዋ ሃገር ሆናለች፡፡

ምድቡን ቀድማ ማለፏን ያረጋገጠችው አልጄርያ በ12 ነጥብ ስትመራ ማሊ በ6 ፣ ማላዊ እና ኢትዮጵያ በተመሳሳይ ነጥብ ተከታዮቹን ደረጃ ይዘው ይከተላሉ፡፡

በኖቬምበር ወር የሚደረጉት የመጨረሻ ሁለት ማጣርያዎች ከአልጄርያ ቀጥሎ የሚያልፈውን ቡድን ይለያሉ፡፡

ያጋሩ