አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ የሦስት ወር ዕግድ ተላለፈባቸው

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ የዲሲፕሊን ውሳኔዎችን አሳልፏል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ጥር 10 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።


የሻሸመኔ ከተማው ዋና አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ክለቡ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በነበረው የ10ኛ ሣምንት ጨዋታ ከተጠናቀቀ በኋላ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት አስተያየት “አሠራርን የሚተች እና የጨዋታ አመራሮችን ክብር የሚነካ አስተያየት ስለመስጠታቸው ሪፖርት ቀርቦባቸዋል።” ያለው የውድድር እና ስነስርዓት ኮሚቴ አሰልጣኙ ላይ የሦስት ወር ዕግድ እና ተጨማሪ የ10ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት መወሰኑን አሳውቋል።