በጋና አስተናገጅነት በሚደረገው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ላይ ኢትዮጵያዊቷ ዳኛ ተመድባለች።
የ2023/24 የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ከፊታችን የካቲት 30 ጀምሮ በጋና አስተናጋጅነት በአክራ ከተማ መደረግ ይጀምራል። በውድድሩ ላይ ኢትዮጵያ በሴቶች ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኗ የምትወከል ሲሆን ከሀገራችን ተሳትፎ በተጨማሪ ካፍ በውድድሩ ላይ በዳኝነት እንድታገለገል አንድ ኢንተርናሽናል ዳኛን በብቸኝነት መርጧታል።
ከፌደራል ዳኝነት ባሳለፍነው ዓመት የፊፋን ባጅ ያገኘችው ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ሲሳይ ራያ በዚህ ውድድር ላይ በዳኝነት እንድታገለግል የተመረጠችው አርቢትር ናት። አርቢትሯ የፊታችን ዕሁድ ወደ ስፍራው እንደምታመራም ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል።