አጋማሹን የውድድር ዓመት በወልቂጤ ከተማ ያሳለፈው አጥቂ ወደ ሌላኛው የሊጉ ክለብ አምርቷል።
ከቀናት በፊት በተከፈተው የውድድር አጋማሽ የዝውውር መስኮት እንደ ወትሮ ሁሉም ባይሆኑም በጣት የሚቆጠሩ ክለቦች ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ። በዘንድሮ ዓመት ከታችኛው የሊግ እርከን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያደገው ሻሸመኔ ከተማም በ15 ጨዋታዎች 9 ነጥብ ብቻ በመያዝ የተጫወተው የጨዋታ ቁጥር ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን በሁለተኛው ዙር ተሻሽሎ ለመቅረብ ዛሬ መስኮቱን መጠቀም ጀምሯል።
በዚህም አጥቂው ስንታየሁ መንግሥቱን የግሉ አድርጓል። የቀድሞ የወላይታ ድቻ ፣ ሀላባ ፣ አርባምንጭ እና ባህር ዳር ከተማ አጥቂ ክረምት ላይ ወደ ወልቂጤ ከተማ አምርቶ የነበረ ሲሆን በስምምነት ከክለቡ ጋር ተለያይቶ ሻሸመኔ ከተማን ተቀላቅሏል።
በተያያዘ ክለቡ ከታምራት ስላስ ፣ ሙሉቀን ታሪኩ፣ ፉዓድ መሐመድ እና ተመስገን ተስፋዬ ጋር በስምምነት መለያየቱ ተጠቁሟል።